የመስቃን ወረዳ ወረዳ ደንና አካባቢ ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
አቶ አወል
የመስቃን ወረዳ ወረዳ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
ራዕይ
በ2022 ዓ.ም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በወረዳው ተገንብቶ ለኑሮና ለስራ ምቹ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት፤
ተልዕኮ
የአካባቢ፣ ብዝሀ-ሕይወትና የደን ሃብት አያያዝ፣ ልማትና አጠቃቀም ለዛላቂ ልማትና ለድህነት ቅነሣ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሥርዓትን የማዘጋጀትና ተፈፃሚነቱን የማረጋገጥ፣ ምርምርና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ሽግግርን የማስተባበርና የማካሄድ፣ ትምህርትና ግንዛቤን የማስፋፋት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ትግበራን የማስተባበር፣ የተግባሪዎችን አቅም የመገንባት፣ የደን ኢንቨስትመንትንና ግብይትን የማስፋፋት፣ ሀገሪቷ የተፈራረመችባቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ የደንና የብዝሀ-ህይወት ስምምነቶችን መተግበር እና ወቅታዊ የአካባቢ እና የደን ሁኔታና ለውጥ ዘገባን የማዘጋጀት ተግባራትን ማከናወን፤
የብዝሃ-ህይዎት ዋና የስራ ሂደት
- የብዝሀ-ህይወት ሃብትና ተያያዥ የማህበርሰብ ዕውቀቶችን በዘቦታና ኢዘቦታ የማንበር ሽፋን ማሳደግ
- በአካባቢና በብዝሃ-ህይዎት ሀብት ላይ ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት መቀነስ
- የመረጃ ና ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ሽግግርን ማሳደግ
- የዘርፉን የመሰርተ ልማት ሽፋን ማሳደግ
- ዘርፉ ለአገራዊ እድገት የሚያበርክተውን ድርሻ ማሳደግ
- የተመናመኑና በመጥፋት ላይ ያሉ የብዝሀ-ህይወት ዝርያዎችን መተካትና መልሶ ማልማት
የአካባቢ ጥበቃ ዋና ስራ ሂደት
- ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ትግበራና የሙቀት አማቂ ጋዝ ሊቀትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራት በተግባሪ ተቋማት ደረጃ መሠራቱን መከታል እና ማረጋገጥ ፣
- የአካባቢ ህግ ተከባሪነት ስርዓት ማጎልበት
- የአካባቢ ደህንነት መብቶችን በማስከበር ዜጎች በንጽህና ጤናማ አካባቢ እንዲኖሩነ ማስቻል
- ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ለመተግበር የሚያስችል የአቅም መገንባት እና አሳታፊ ዘርፍ አቀፍ የማጣጣሚያ መርሀ- ግብሮችን ማከናወን
- የደንና የጥበቃ ቦታዎችን ማሻሻል
- የወረዳው የደን ሃብት በዘላቂነት በመጠበቅና በመንከባከብ ጠቀሜታቸው ያደገ ስነ ምህዳር መፍጠር
- የአካባቢ ህግ ተከባሪነትን ስርዓት ማጎልበት
- የወጣቶችና ሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ
- የዘርፉን የመሰረተ ልማት ሽፋን ማሳደግ
- ዘርፉ ለአገራዊ ኤኮኖሚ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ
አገራዊ የደንና የጥብቃ ቦታዎች ሽፋንን ማሳደግ፣
በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose
ዓላማ
- በወረዳ ደረጃ እየመጣ ያለው ፈጣን እና ፍትሐዊ ልማት ዘላቂና አካባቢያዊ ደህንነትን ያረጋገጠ እንዲሆን ማስቻል፣
- በ2022 ሀገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው እንቅስቃሴ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስልት ትግበራ በወረዳ ደረጃ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ማበርከት፤
- የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀምን በማሻሻል ከደን ሀብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ምህዳራዊ አስተዋጽኦ ማሳደግ፤
- የብዝሃ-ሕይወት ሀብት የሚጠበቅበት፣ የሚለማበት፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውልበትና ፍትሃዊ የጥቅም ተጋሪነት የሚኖርበት ሁኔታ ማመቻቸት፣
እሴቶች
- ለተገልጋዮች ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት፤
- የተፈጥሮ ሀብታችንና አካባቢያችንን መንከበከብ፤
- የለውጥ ኃይሎችን ማበረታታት፤
- ህብረተሰቡን በልማት ማሳተፍ፤
- ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፤
- ሙያዊ ሥነ-ምግባር ማስፋፋት፤
- ፍትሃዊነት፤ ሰብአዊነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፤
- ለሀገር በቀል ዕዉቀት እዉቅና መስጠት፤
- የሴቶችና የወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
- መረጃን ለልማት ማዋል፤
