የመስቃን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

576756142 1147806017540859 661907253090341029 n

ረ/ኢ አብድረሂም ህያር

የመስቃን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ

አላማ

በክልላችን ፣በዞናችን ፣በወረዳችን የተጀመረው የልማት  ዕቅድ  የዴሞክራሲ  ስረዓት  ግንባታ  ለማፋጠን  ሁለንተናዊ  የማሰፈጸም  አቅምን  በመገንባት  ተቋማት  ለተልዕኳቸው   ብቁ   እንዲሆኑ  ማደረግ  ይ ፡፡ለዚህም  አፈጻጸምን   ሚዛናዊ  በሆነ    እይታ  እና  ምክኒያታዊ በሆነ  ውጤት  አስተሳስሮ  መምራትና  የሚፈለገውን   ውጤት  ከበጀት  ጋር  አጣጥሞ  በተግባር  የማዕከሎች  ማሳደግና   ስትራቴጅያዊ  ግቦችን ወደ  አመታዊ  ግብና  አብይት ተግባር እንዲሁም ወደ የዕለት ተዕለት ዝርዝር ስራዎች በመቀየር መፈጸም ማስቻል ፡፡

ተልዕኮ

የወረዳው   የቀበሌው   ህገ-መንግስት እና ሌሎች ህጎችን በማክበርና በማስከበር ህብረተሰቡን በማሳተፍ ወንጀልን መከላከል ተፈጽሞ ሲገኝም በጥራትና በፍጥነት በማጣራት ለሚመለከተው የፈትህ አካል ማቅረብ  የአባላት ማስፈጸም አቅም መገንባትና ከሌሎች የፈትህና የጸጥታ ሃይሎችና ከባለ ድርሻ አካለቶች ጋር ቅንጅት በመፍጠር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ መድረግ ነው፡፡

ራዕይ

በዞናችንና  በወረዳችን  የህግ   የበላይነት   ሰፍኖ  የህዝብ ሰላምና  ደህንነት  የተረጋጋጠበትና   ከወንጀልና  ከትራፊክ አደጋ ስጋት ነጻ የሆነ ህብረተሰብ መፍጠር የሚችል ተቋም ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡

ዕሴቶች

  • ለህገ መንግስቱ ታማኝ  መሆን 
  • ከራስ በላይ የሕዝብና  የሀገር  ጥቅምን   ማስቀደም
  • የተስተካከለ ፖሊሳዊ ስብዕና መላበስ
  • በማንኛውም ፖሊሳዊ ተልኮ  የላቀ  ውጤት ማሰመዝገብ 
  • ፅናት፣ መሰዋዕትነትና ሰብዓዊነት መላበስ
  • ብዙሃንነትን መቀበልና ማክበር
  • ለፖሊስ ሙያና አርማ ክብር መስጠት
  • የህዝባችንን ታሳትፎና እርካት  መረጋገጥ
  • የሙያ ሚስጥርን መጠበቅ
  • በጋር የመስራት መርህን  መከተል
  • ግልጸኝነትን ፣ገለልተኝነትንና መልካም አርአያነት
  • ሁል ጊዜም ራስን ማብቃትና  በማንኛውም ተግባር የላቀ ውጤት  ማስመዝገብ