የመስቃን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት

የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

photo 2025 06 29 13 07 01

አላማ

የወረዳችን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ ፖለቲካዊና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በተግባር እንዲሁም አደረጃጀትና የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተደርጎ ህ/ሰቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራትን በመከወን ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ ነዉ፡፡

ተልዕኮ

በወረዳው ያሉትን ሰብአዊና ተፈጥሮዋዊ ሐብቶች አቀናጅቶ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በመምራትና በማረጋገጥ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እድገትን አጠናክሮ በማስቀጠል የወረዳችን ህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

1.በአስተዳደር ድ/ቤት የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና መሰረተ ልማት ጉዳዩች ዋና የስራ ሂደት ዋና ዋና ግቦች

  • በአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዩች እርካታ ማሳደግ
  • የተገልጋዬች የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
  • የበጀት አጠቃቀም ውጤታማነት ማሳደግ
  • የእቅድ አተገባበር ውጤታማነትን ማሳደግ
  • የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ውጤታማነት ማሻሻል
  • እቅዶችን መገምገምና ማረጋገጥ
  • ፈጣን ምላሽ የሚሹ ጉዳዩች በማጣራት ውሳኔ መስጠት
  • የሪፖርት ግምገማና ግብረ-መልስ መስጠት

2.የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም-አካባቢያዊ ጉዳዮች ስራ ሂደት

          ዋና ዋና ግቦች

  • የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎች ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መፍታት
  • በቅሬታ አፈታት ስርኣት ህብረተሰቡ ተሳታፊ ማድረግ
  • በቅሬታ አፈታት ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ትምህርት መስጠት
  • ቅሬታ የሚበዛባቸዉ ጉዳዮች ጥናት ማድረግ
  • እለታዊ የጸጥታ መረጃዎች ማሰባሰብ
  • የሚቀርቡ ቅሬታዎች መመዝገብ
  • የጸጥታ ሴክተሮች እቅድ አፈጻጸም መከታተልና ግብረመልስ መስጠት

በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦችClose

ራዕይ

በወረዳው ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት

እሴቶች

  • የህግ የበላይነት መርሆችን ነው፡፡
  • ለተገልጋይ ፍላጎት ትልቅ ዋጋ እንሰጣለን፣
  • መቻቻል ባህላችን ነው፣
  • አሳታፊነት መለያችን ነው፡፡
  • ፍትሐዊነትና ሚዛናዊነት መመሪያችን ነው፡፡
  • ልዩነታችን ውበታችን፣ ውበታችን አንድነታችን ነው፡፡