ኢሎል

ኢሎል ለአስተዳደራዊ ምቹነት በባህላዊ መንገድ ሹመት የሚሰጥበት ስፍራ ነው።መገኛውም በመስቃን ወረዳ ምዕራብ መስቃን ቀበሌ ውስጥ ከዘቢደር ተራራ ስር የሚገኝ እጅግ ውብ የሆነ በተፈጥሮ እና አገር በቀል እጽዋት የለመለመ ጥንት የተዘጋጁ በድንጋይ የተመቻቹ መቀመጫዎች ያሉት ስፍራ ነው ፡፡ኢሎል በጥንት መስቃን ለአስተዳደር የሚመረጥ የተመረጠ ሰው ሹመት የሚጸድቅመት ቦታ ነው ፡፡በኢሎል ለአስተዳደርነት የሚመረጠው ሰው ለመለየት የጎሳ ሹማምንቶች በሙሉ ይመክሩበታል ።ድማም ፣ ጎሽቶ፣ ገራድ፣ላዝማ ፣ አዝማ ፣ አዝማች፣ ሱልጣን ፣ ኢማም ተብለው የማዕረግ ሹመት ሲሰጣቸው ኢሎል ስፍራ በሚካሄደው የንግስና በዓል እውቅና ይሰጠዋል ።ኢሎል ስፍራ የነገሱ እጅግ ብዙ ቢሆኑም በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቀውና ታሪኩ በስፋት የሚነገርላቸው ከድማም ጀምሮ እስከ ኢማም ናቸው።ድማም በጋሞ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ናቸው በኋላም በህመም ምክንያ አልጋ ላይ ከዋሉ በኋላ ንግስናቸውን ለልጃቸው ቢሰጡትም አሻፈረኝ ብሎዋቸዋል።ድማም በጋሞ እንዳረፉ ደፋሩ ጦረኛ የባዴ ልጅ ጎሽቶ ቀለምሶ ነገሰ ፡፡ የባለቤታቸውንም ጊስቶ የሚል የነግስና ስም ሰየመ ፡፡ በኋላም በአመታዊ ክብረ በአል ላይ ጎሽቶ ቀለምሶ በመሸነፍ ሀፍረት ተሰምቶት ሸሸ መንበረ ስልጣኑን ለሻዶ ልጅ ገራድ ባለከሽ አስረክበ ።ገራድ ባለከሽም የባለቤታቸውን ስም “ጊስቶ” የሚለውን በመሻር ” ኢቴ ” የሚለውን ለሴቶች የንግስና ስም ሰየሙ ፡፡ ዛሬም ድረስ በመስቃን ማህበረሰብ ይህ መጠሪያ ለሴቶች የንግስና መጠሪያ ስም ነው ።ሸሽተው የነበሩ ባዴና የባዴ ልጆች ከባዴ ህልፈት በኋላ ተመልሰው መጥተው ስልጣን ይገባናል ብለው የማጋውን የዳኝነቱን ስርአት እንዲመሩት ተደረገ እስከ ኢማም በድሩ ድረስ የማጋውን ስልጣን በባዴ ዘር ነው የነበረው።ገራድ ካለፉ በኋላ የሳቸው አራተኛ ትውልድ የሆነው ላዝማ ማሬኖ ንግስናውን ተቀባ ፡፡ ላዝማ ማሬኖ ለረዥም ዘመን በንግስና ስማቸው የቆዩ ናቸው ፡፡ የላዝማ ወዳጅ ሼህ ኡስማን የነበሩት የራጋ ዳኝነትቱ ወይም በአሁኑ አጠራሩ ሰበር ሰሚ ችሎቱን(ፈራገዘኘ የባህላዊ የዳኝነት እና እርቅ ) ተሰጣቸው እውቀት ብቻ ሳይሆን ፍትሀዊም ነበሩ ። ከላዝማ ማሬኖ በኋላ አዝማ ሳሊሶ ተተኩ። አዝማ ሳሊሶ ጦረኛም ጠቢብም ነበሩ ይባላል ።
ይበልጥ ያንብቡ
474890141 589006057393783 5022346653761667192 n
481997849 956139116707551 5417833706346052507 n
475744380 590823373878718 1071699610116090895 n
481970720 956139420040854 2364702690804555054 n