የመስቃን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
ትምህርት በሀገር ስልጣኔም ሆነ ኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣው ለውጥና ተፅዕኖ ቀላል እንዳልሆነ ከሁላችንም አዕምሮ የማይጠፋ ሀቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጲያ ባሳለፍናቸው ኣመታት በትምህርት ልማት ዘርፍ ፕሮግራሞች የትምህርት ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር እጅግ በጣም ጥሩ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ከጥራት አኳያ ሲታይ ሰፊ ውስንነቶች የነበሩበት መሆኑ በተጨባጭ በእስታንዳርድ ፈተናዎች እያስመዘገብነው ያለው ውጤት አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በወረዳችን የትምህርት ፖሊሲው ከመቀረፁ በፊት የነበረው የትምህርት ሽፋን ፖሊሲው ከተቀረፀ በኃላ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት የነበረው ነው፡፡ በዚህም ከትምህርት ፍትሐዊነትና ተደራሽነት አንጻር የቅድመ አንደኛ ትምህርት ለመስጠት በግል (የአጸደ ህጻናት ብዛት 11 ሜርሲ ፕሮጀክትን ጨምሮ ፣በመንግስት በመጀመሪያና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ የቅድመ 1ኛ ብዛት 54 እና ከግቢ ውጪ ብዛት 4 በድምሩ 58 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተቋማት(1-6) ብዛት 11፣ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ የትምህርት ተቋማት (1-8) ብዛት 43 (ሜርሲ ፕሮጀክትን ጨምሮ) ፣ የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ተቋማት (9-12) ብዛት 9 በአጠቃላይ የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት 74 ማድረስ የተቻለ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን (ከ1ኛ – 12ኛ ) የክፍል ደረጃ 26154 ተማሪዎች ለመቀበል ታቅዶ 23198 መደበኛ ተማሪዎች ቅበላ የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 89% ይህም ከ2016 ዓ.ም የቅበላ አፈፃፀም አንፃር ሲታይ የ4% ጭማሪ ያለው ቢሆንም ከእቅዳችን አንፃር ግን 11% ወደ ትምህርት ቤት ያልገቡ ተማሪዎች መኖራቸው በውስንነት የተገመገመ ሲሆን የተቀበልናቸው ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን በተገቢው እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በህዝባችን የልዩ ፍላጎት ጉዳት ያለባቸው ህፃናት ማስተማር ገመናን እንደ ተደርጎ ይቆጠር ከነበረው የተሳሳተ አመለካከት ወጥቶ ድጋፍ የሚሹ ህፃናትን ወደ ት/ቤት እንዲገቡ በተደረገው የንቅናቄ ስራ ከ1-12 ክፍል 863 ለዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ለመቀበል ታቅዶ 764 ተማሪ በመቀበል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
አቶ ከድር ሁሴን
የመስቃን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ
ራዕይ
በወረዳዉ ፍትሀዊነቱናጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በማድረስ በእውቀት፣በክህሎትና በአመለካከት የተስተካከለና ለልማት፣ለፍትህ፣ለሠላምና ለዲሞክራሲ ግንባታ የላቀ ሚና የሚጫወትናበገበያ ላይ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ተፈጥሮ ማየት፡፡
ተልእኮ
ፍትሀዊ፤ አካታች እና ተደራሽ የሆነ ጥራቱና አግባብነቱ የተረጋገጠ በመልካም አስተዳደር ላይ የተገነባ የህይወት ዘመን ትምህርትና ስልጠና አካል የሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ለዜጎች ማቅረብ!!
እሴት
- ሃገር ወዳድነት
- የባለቤትነት ስሜት
- ብቃትና ዉጤታማነት
- ፍትሃዊነት
- ግልጸኝነትና ተጠያቂነት
- የሃይማኖት እኩልነት
- የህዝብ ጥቅም ማስቀደም
- መከባበር፣ሀቀኝነት፣መቻቻል
- ሁሌም ለትምህርት ጥራት፣ መስራት
- ለለውጥ ዝግጁ መሆን፣
