የመስቃን ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
አቶ ሙሰማ ጀማል
የመስቃን ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ
አላማ
የጽ/ቤቱ ስትራቴጂያዊ መሠረቶችንና የትኩረት መስኮችን አንጥሮ መለየትና በቀጣይም በየደረጃው የሚገኙ ፈጻሚ አካላት፣የስራ ሂደቶችና ፈፃሚዎች ከጽ/ቤቱ ስትራቴጂ የየራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ማቀድና መተግበር የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠርና የውጤት ተኮር ስርዓት ለመዘርጋት ነው፡፡
ተልዕኮ
አሰራርና አደረጃጀትን ዘመናዊ በማድረግ፣ ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ሥርዓት በመፍጠር፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገዝና ብቃት ያለው የፀጥታ ኃይል በማፍራት ግጭትን፣ በሃይማኖት ወይም እምነት ሽፋን የሚፈጸም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከትን በብቃት በመመከትና በመከላከል የወረዳውን ፀጥታ፣ ሠላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግሥቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣
የሰላም አሴት ግንባታ
- በግጭት መከላከል መፍታትን በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ ህብረተሰብ ግንዛቤ መፍጠር
- በግጭት መከላከል መፍታትና በሰላም እሴት ግንባታ ባለድርሻ አካላትና ተባባሪ ወገኖች ግንዛቤ መፍጠር
- የወረዳው የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያን ፈጣን ምላሽ የሁኔታ መከታተያ ክፍል እንዲጠናከር ማድረግና የሁኔታ መከታተያ ክፍል የተቋቋመውን ይጠናከራል፣
- አንድ ወረዳዊ በወረዳ የግጭት አዝማሚያ ትንተና ሰነድ ማዘጋጀት
- በግጭት መከላከልና መፍታት ዙሪያ በተመረጡ አካባቢዎችና ጉዳዮች ላይ ጥናት ማካሄዱ፣
- ከወረዳ በላድርሻ አካላትጋር የመረጃ ልዉዉጥና የግ/መልስ ስራዎች መከናወ
የፀጥታ መረጃና አሰባሰብ አስተዳደር
- በወረዳው ከፀረ–ሰላም ሀይሎች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የፀጥታ ስጋቶችን በመለየት አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ትኩረት በተደረገባቸው ጉዳዩች ላይ የጸጥታ ስጋት መረጃ መሰብስብ
- የፀረ ሰላም ሀይሎችጉዳት/አደጋ ለማድረስ ትኩረት በሚያደርጉባቸው ጉዳዮች ላይ በየጊዜው የደረሰበት ደረጃ (progress) ክትትል ማድረግ
- የቀረቡ መረጃዎችን ውሳኔ ሠጪ አካላት እንዲጠቀሙ በማንቃትና ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ የፀጥታ ስጋቶችን እንዲመክኑ ማድረግ
የፀረ–ሰላም ሀይሎች እንቅስቃሴ በማምከን የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ
- በወረዳው ከህገ ወጥ ድርጊቶችና የተደራጁ ወንጀሎች ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል የፀጥታ የስጋትና አመላካች መረጃዎች መሰብሰብ
- በህገወጥ ድርጊትና በተደራጁ ወንጀል እንቅስቃሴዎች በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት/አደጋ እንዳይደርስ በየጊዜው ያሉበትን የፀጥታ ሁኔታ ክትትል ማድረግ
- የቀረቡ መረጃዎችን ህብረተሰቡንና ውሳኔ ሠጪ አካላት በማንቃት ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ የፀጥታ ስጋቶችን እንዲመክኑ ማድረግ
ህገ –ወጥ ድርጊቶችንና የተደራጁ ወንጀሎች ላይ ወቅታዊ መረጃችን በማቅረብ የህብረተሰቡን ስጋት መቀነስ
የቴክኖሎጂና የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችን ተከታትሎ በማቅረብ የተገልጋዩን የመረጃ ፍላጎት ማሳደግ
- በቴክኖሎጂ ውጤቶችና በሚዲያዎች የሚሠራጩ ህብረተሰቡን ላልተፈለገ አመፅና ሁከት ሊያነሳሱ የሚችሉ መልዕክቶችን በመከታተል መረጃዎችን መሠብሰብ
- የፀረ ሰላም ሀይሎች ትኩረት በሚያደርግባቸው ጉዳዮችን የቴክኖሎጂ እና ማህበራዊ ሚዲያ ውጤቶችንበየጊዜው ክትትል ማድረግ
- በቴክኖሎጂ እና በማህበራዊ ሚዲያ ውጤቶች የሚሠራጩህብረተሰቡ ለአመፅና ለሁከት የሚዳርጉየጸረ– ሠላም ሀይልመልዕክቶችን ተከታትሎ ለውሳኔ ሠጪ አካላት በማቅረብ የፀጥታ ስጋቶችን እንዲመክኑ ማድረግ
የፀጥታ ስጋት ዳሰሳ እና ጥልቅ ጥናት በማድረግ የፀጥታ መረጃ ውጤታማነት ማሳደግ
- የወረዳውን የፀጥታ ስጋት ሁኔታ ችግሮችንና ክፍተት በመለየት ተዛማጅ መረጃዎችን በማሠባሰብና ጥናት በማካሄድ ግብዓቶችን አካቶ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
- የወረዳውን የፀጥታ ስጋት ሁኔታ ለማጥናት ፕሮፖዛል አዘጋጅቶ በማስተቸት ግብዓት አካቶ መረጃዎችን በመሰብሰብና በማጠናቀር የፋይዳ /ጥልቅ/ ጥናት ማካሄድ
- የተካሄዱ የዳሰሳ ጥናት ሠነድ እና ጥልቅ ጥናት ሠነዶች ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ
የባለድርሻ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር ውጤታማነት ማሳደግ ዋና ዋና ተግባራት
- ለፀጥታ ስራ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ባለድርሻ አካላት ከህብረተሰቡ ውስጥ መመልመል
- ከባለድርሻ አካላት ወይም ከህብረተሰቡ የተመለመሉ የመረጃ ምንጮች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን መዘጋጀት
- ከሚመለከታቸው ስራ ሂደቶችና ተቋማት ጋር በስራ ዙሪያ ለሚደረጉ የጋራ ግንኙነት ለማጠናከር የመግባቢያ ሠነዶችን አዘጋጅቶ ማቅረብ
ዘመናዊ የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመዘርጋት ቅልጥፍናን ማሳደግ
- በየሳምንቱ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የጸጥታ መረጃዎችን ሪፖርት በሶፍት ኮፒ ማደራጀት
- መረጃዎችን ለመሰብሰብና ሪፖርት ማድረጊያ የሚያስችሉ የተለያዩ ዓይነትና ይዘት ያላቸው ወቅታዊ ቅጻ ቅፆችንና መዛግብቶችን አዘጋጅቶ ወቅታዊ ማድረግና መጠቀም
በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose
ራዕይ
የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር፣ የህዝቡ ሠላም፣ ፀጥታና ደህንነት የተረጋገጠበት ወረዳ ተፈጥሮ እና ለዚህም የበኩሉን ጉልህ ድርሻ የሚያበረክት ሴክተር ሆኖ ማየት፣
ዕሴት
ዕሴቶች የሴክተሩ ሠራተኞችና የሥራ አመራሩ የሚመሩባቸውና ወደፊትም በጋራ ሊከተሏቸው የሚገቡ የግልና የተቋም የአሰራር ፍልስፍናዎች ሲሆኑ ሴክተሩ፡-
- ለህገ-መንግሥቱ ታማኝ መሆን፣
- የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥ፣
- ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣
- የሕዝብ አገልጋይነት፣
- ብዝሃነት መቀበልና ማክበር፣
- ፍትሃዊነትና ሰብአዊነትን መላበስ፣
- ራስን ማብቃት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ማወቅና መጠቀም፣
- ሙያዊ ሥነ ምግባር መላበስ፣
- ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ትኩረት መስጠት እና
- ኃላፊነትን መወጣት የሚሉት ናቸው፡፡
