የመስቃን ወረዳ ፕላን ኮሚሽን ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
ወ/ሮ አይናለም ተመስገን
የመስቃን ወረዳ ፕላን ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
ራዕይ
ፍትሃዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የወረዳዉ ሕዝብ ከድህነት ተላቆ ማየት፡፡
ተልዕኮ
በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መለስተኛ ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በወረዳዉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡
1/ስነ-ህዝብ ዳሬክቶሬት ዋና ዋና
የስነ-ህዝብ ና ልማት ዳሬክቶሬት ዋና ዋና ተግባር፤
- ከተገልጋይ እይታ አንጻር
ግብ1.1 የተገልጋዮች መረጃ ፍላጎት በማሟላት እርካታን ማሳደግ
- ባለድርሻ አካላት የሥነ ህዝብና ልማት መረጃን ማሠባሠብ በመተንተንና ለተገልጋዩ ማሠራጨት፤
- በስነ-ተዋልዶ፤በሥርዓተፆታ፤ኤች.አይ.ቪ ኤድስና ሥነ ህዝብ አስመልክቶ ለባለድርሻ ሴክተር መ/ቤቶች በየሩብ ዓመቱ ብሮሸር ማሰራጨት፤
- የስነ ህዝብ ክበበት ውጤታማነት በጥናት መለየት
- ባለድሻ አካላትን በማሳተፍ የጥናት መረጀዎቸን ማሰባሰብ
- የጥናቱ ውጤቱን በባለድርሻ አካለት ጋር ማስተቸትና ሰነዱን ማዳበርና ይፋ ማድረግ
2//የሶሺዮ ስራ ሂደት
- የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ግቦች
ሀ. ከተገልጋይ እይታ አንፃር፣
ግብ 1. የስታትስቲክስና መልካ-ምድራዊና የካርታ መረጃን ተደራሽ በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ
- የተገልጋይን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የስታትስቲክስ መረጃዎችን በማዘጋጀት በሀርድና ሶፍት ኮፒ በማደራት በመረጃ መረብ ለተገልጋዮች ተደራሽ በማድረግ እርካታቸውን ማሳደግ፣
- የተለያዩ የሶሺዮ-ኢኮኖሚክ መረጃዎችና የድህነት ቀናሽ ሰክተሮች መረጃ) በብሮ`ር መልክ የተዘጋጁ ዶክመንቶችን በሀርድና ሶፍት ኮፒ ተደራሽ በማድረግ እርካታቸውን ማሳደግ፣
- የተደራጀ ሀብት ክፍፍል ግብአት የሚያስፈልግ የቀመር አመልካች መረጃ በማቅረብ እርካታቸውን ማሳደግ፣
- ከሴ/መ/ቤት መረጃ ለሚጠይቁ መንግስታዊ የበጎ አድራጎት ማህበራትና የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች የምርምር አካላት መረጃ ፈላጊዎች አገልገሎት በመስጠት እርካታቸውን ማሳደግ፣
- ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት በስራ ሂደት ለውጥ ጥናት ላይ ለስነ-ህዝብና ልማት ስራዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት በመስጠት እርካታቸውን ማሳደግ፣
ለ. ከፋይናንስ ዕይታ አንጻር
ግብ 2. የሃብት አጠቃቀም ውጤታማነትን መጨመር
የበጀት አፈጻጸም ውጤታማ ማድረግ
በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose
እሴቶች
- ቆጣቢነት
- ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
- ፍትሃዊነት
- ውጤታማነት
- በእቅድ መመራት
- ሕጋዊነት
- ቀልጣፋ አገልገሎት
- ተቆርቋሪነት
- ግልፀኝነትና
- ተጠያቂነት
