የመስቃን ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
ዓላማ
የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ዋነኛ አላማ ለወረዳው ልማትና መልካም አስተዳደር ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል ከወረዳው የኢኮኖሚ እድገት ጋር የተመጣጠነ የልማት ገቢ መሰብሰብ ነው፡፡ ይህንን ታላቅ አላማ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ አሰራሩን ይበልጥ በማጠናከር የተገልጋዩን ህብረተሰብ ፍላጎት ለማርካት ፈጣን የሆነ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲቻለው በክልል ደረጃ የመሰረታዊ ስራ ሂደት ለውጥ ጥናት ተካሂዶ የጥናቱም ግኝት ዕውን ማድረግ የሚያስችል እቅድ ተነድፎ ወደ ተግባር ገብቶ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በአሰራሩ መሻሻያ ከተገልጋዩ በጎ ምላሽ እያገኘ ይገኛል፡፡
የገቢ አሰባሰብ ዋና ዋና ተግባራት
- የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነት ማሳደግ
- የአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸምን መሻሻል
- ጠቅላላ ወረዳዊ ገቢ ማ
- የታክስ ህግ ተገዥነት አፈጸጸም ማሻሻል
- የመረጃ ቴክኖሎጄ ሀብት እና አጠቃቀምን ማሻሻል
- የታክስ እና አገልግሎት ቅሬታ አፈታት ስራት አፈጻጸም ማሻሻል
- ፍቃደኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር ማሳደግ
- ግዴታቸውን በፈቃደኝነት የሚወጡ ግብር ከፋዮች ቁጥር ማሳደግ
- ከግብርና ሥራ የሚሰበሰበውን ገቢ ማሣደግ
- ከጫት የሚሰበሰበውን ገቢ ማሳደግ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ግብር ከፋዮች ቁጥር ማሳደግ
- የተርን ኦቨር ታክስ ግብር ከፋዮች ብዛት ማሳደግ
- የግብር ከፋዮችን ብዛት ማሳደግ
- የገቢ መረጃ አስተዳደረና አጠቃቀመ ሥርአት ማሻሻል
- የገቢ መረጃ መሰረተ ልማት ማስፋፋት ደህንነትና አጠባበቅ ሥርዓት ማሻሻል
- የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ሥርዓት ማሻሻል
- የሰው ሀይል ብቃትንና ውጤታማነትን ማሳደግ
- የሠራተኛውን አመለካከትና ሙያዊ ሥነ ምግባር ማሳደግ
- የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዕውቀትና ክህሎት ማሳደግ
የታክስ ትምህርት እና ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶሬትዋና ዋና ተግባራት
- የተገልጋይ እርካታና አመኔታ ማሳደግ
- የትምህርትና የሕዝብ ግንኙነት ሥርዓት ማሻሻል፣
- የፊት ለፊት የታክስ/ግብር ሥልጠናና ግንዛቤ ያገኙ ግብር ከፋዮች ቁጥር ማሳደግ
- የክህሎት ስልጠና ያገኙ ግብር ከፋዬች ቁጥር ማሳደግ
- የቤት ለቤት ድጋፋዊ ከትትል ተደረገባቸው ግብር ከፋዮች ብዛት ማሳደግ
- የተገልጋዮች አገልግሎት እና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት ማሻሻል፣
- የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት ማጠናከር
- የግብር ስወራና ማጭበርበር መከላከል የሚያስችል የአሠራር ሥርዓቶች ማሻሻል፣
- የባለድርሻ አካላት አጋርነትና ትብብር ማሻሻል
- ምርጥ ተሞክሮዎች መቀመርና ማስፋፋት
- የክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት ማሻሻል
.
በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose
ራዕይ
በዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ተገንብቶ ኢኮኖሚዉ ከሚያመነጨዉ ሀብት ሙሉ በሙሉ ገቢ ተሰብስቦ ለልማት ዉሎ ማየት
ተልዕኮ
ሁለንተናዊ አቅሙ የተገነባ ተቋም እና የሰዉ ኃይል በማፍራት ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፣ የተጣጣመ ሀገራዊ ፣ ክልላዊ ፣ ዞናዊ እና ወረዳዊ የታክስ አስተዳዳር ሥርዓት በመገንባት ፣ ፍትሀዊ፣የላቀ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት በመስጠት፤ ታክስ በፍቃደኝነት የመክፈል ባህልን በማዳበር፤ የታክስ እና የገቢ ህግጋትን በማስከበር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ መሰብሰብ”
እሴቶች
- አገልጋይነት
- አገልግሎትን በጊዜና በጥራት በመስጠት በልጦ መገኘት
- ሙያና ክህሎትን ለተጨባጭ ውጤት መጠቀም /Professionalism/
- ታማኝነት
- ተጠያቂነት
