የመስቃን ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
ራዕይ
በ2022 በወረዳው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጠብቀው የህግ የበላይነት ተረጋግጦ በአገራችን፣ በክልላችን በዞናች ብሎም በወረዳችን በአርአያነት ሊጠቀስ የሚችል ፍትህ ሰፍኖ ማየት፡፡
ተልዕኮ
በወረዳው ፍትህ እንዲሰፍን፣ የመንግስትና የህዝብ ጥቅሞች እንዲጠበቁ፣ በህገ-መንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ማስቻል፤ የህብረተሰቡን ንቃተ-ህግ በማሳደግ፣ ወንጀል ፈጻሚዎች ለህግ እንዲቀርቡና ለፈጸሙት ጥፋት በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ፣ የዜጎችን የመደራጀት መብት ማረጋገጥ፣ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎቸን መስጠት፤ የህግ ታራሚዎች ብቁና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ የማረምና የማነጽ የመሪነት ሚናን በመጫወት መልካም አስተዳደርን ማስፈን ነው፣
- የወንጀል ጉዳዮች አስተዳደር አፈጻጸም ውጤታማነት ማሳደግ
- የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች አስተዳደር ጥራት እና ውጤታማነት ማሳደግ
- የወንጀል ምርመራ ሥራ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት በመስራት ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፖሊስ የሚመለሱ መዝገቦች አሁን ካለበት ‹1% ወደ 0% መቀነስ እንዲሁም ምስክርና ማስረጃ በመጥፋት የሚቋረጡ የወንጀል ክስ መዝገቦች የመቋረጥ ምጣኔ ካለበት 6.3 % ወደ 5.5% ለመቀነስ በትኩረት ይሰራል፤
- ለዐቃቤ ህግ የሚቀርቡ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች የማጥራት ምጣኔን አሁን ካለበት 94.8% 99%፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ከተሰጠባቸው መዝገቦች መካከል የማስቀጣት ምጣኔን በመዝገብ ካለበት ከ95% ወደ 100% እንዲሁም በተከሳሽም 95% ለማድረስ ይሰራል፤
- በዕርቅ ማለቅ የሚገባቸው ቀላል የወንጀል መዝገቦች አፈጻጸም 44.25% ማድረስ
- ዐ/ህግ ህግ ይግባኝ በጠየቁባቸው መዝገቦች የፍርድ ቤት ውሳኔን እንዲሻር ወይም እንዲሻሻል የማድረግ ምጣኔ በመዝገብ አሁን ያለበትን 1ዐዐ% ማሳካት እንዲሁም በተከሳሽም አፈጻጸሙን 1ዐዐ% ማሳካት ሲሆን የሰበር በመዝገብ ወደ 95% እና በተከሳሽ 82% ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፤
- ተከሳሾች ይግባኝ የጠየቁባቸው ጉዳዮች የፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲጸና ወይም እንዲሻሻል የማድረግ አቅም በመዝገብ አሁን ካለበት 95% ወደ 95% እና በተከሳሽ 91% እንዲሁም ሰበር በመዝገብ 96% እና በተከሳሽ 91% እንዲደርስ ይደረጋል፤
- የሙስና ወንጀሎች አስተዳደር ጥራት እና ውጤታማነት ማሳደግ
- የወንጀል ምርመራ ሥራ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት በመስራት ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፖሊስ የሚመለሱ መዝገቦች አሁን ካለበት 1ዐ% ወደ 2% ለመቀነስ እንዲሁም ምስክርና ማስረጃ በመጥፋት የሚቋረጡ የወንጀል ክስ መዝገቦች የመቋረጥ ምጣኔ በ2017 በጀት ዓመት ወደ 5.5% እንዲቀንስ ይሰራል ተብሎ የታቀደ ሲሆን አፈጻጸሙ ወደ 1% ማውረድ የተቻለ ሲሆን ይህን በቀጣይም አጋማሽ ለማሳካት በእቅድ ተይዟል፣
- ለዐቃቤ ህግ የሚቀርቡ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች የማጥራት ምጣኔን ወደ 94.8% ከፍ ለማድረግ በእቅድ ተይዞ አፈጻጸም 99% የተሳካ ሲሆን የቀጣይ እቅዳችን አድርገናል፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ከተሰጠባቸው መዝገቦች መካከል ጥፋተኛ የማሰኘት ምጣኔን በመዝገብ ከ96.6% ወደ 98% እንዲሁም በተከሳሽ ደግሞ ከ94.9 ወደ 95% ለማድረስ ይሰራል፤
- ዐ/ህግ ይግባኝ በጠየቁባቸው መዝገቦች የፍርድ ቤት ውሳኔን እንዲሻር ወይም እንዲሻሻል የማድረግ ምጣኔ በመዝገብ ወደ 78% እና በተከሳሽ 82% እንዲሁም የሰበር መዝገብ 75% እና በተከሳሽ 82% ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፤
- ተከሳሽ ይግባኝ የጠየቁባቸው ጉዳዮች የፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲጸና ወይም እንዲሻሻል የማድረግ አቅም በመዝገብ 91% እንዲሁም በተከሳሽ 91%፣ ሰበር በመዝገብ ወደ 90.5% እና በተከሳሽ 91% እንዲደርስ ይደረጋል፤
- በሙስና የተመዘበረ የመንግስት ሀብትና ንብረት የማስመለስ ምጣኔ ወደ 100% የማሳደግ ስራ ይሰራል፡፡
- የታክስ ነክ ወንጀሎች አስተዳደር ጥራት እና ውጤታማነት ማሳደግ
- የወንጀል ምርመራ ሥራ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት በመስራት ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፖሊስ የሚመለሱ መዝገቦች አሁን ካለበት 3.5% አፈጻጸም ወደ 3.5% ዝቅ ለማድረግ እንዲሁም ምስክርና ማስረጃ በመጥፋት የሚቋረጡ የወንጀል ክስ መዝገቦች የመቋረጥ ምጣኔ ከ7.7% ወደ 5.5% እንዲቀንስ በትኩረት ይሰራል፤
- ለዐቃቤ ህግ የሚቀርቡ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች የማጥራት ምጣኔን አሁን የምንገኝበትን 1ዐዐ% ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ከተሰጠባቸው መዝገቦች መካከል ጥፋተኛ የማሰኘት ምጣኔን በመዝገብ 96% እና በተከሳሽ 91.5% ለማሳካት በእቅድ የተያዘ ሲሆን አፈጻጸሙን 1ዐዐ% ማሳካት የተቻለ ሲሆን ይህንኑ አፈጻጸም ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፣
- ዐ/ህግ ይግባኝ በጠየቁባቸው መዝገቦች የፍርድ ቤት ውሳኔን እንዲሻር ወይም እንዲሻሻል የማድረግ ምጣኔ በመዝገብ 87% እና በተከሳሽ 82% እንዲሁም የሰበር በመዝገብ 75% እና በተከሳሽ 82% ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፤
- ተከሳሽ ይግባኝ የጠየቁባቸው ጉዳዮች የፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲጸና ወይም እንዲሻሻል የማድረግ አቅም በመዝገብና በተከሳሽ 91% እንዲሁም ሰበር በመዝገብ 90% እና በተከሳሽ 91% እንዲደርስ ይደረጋል፤
- በታክስ ማጭበርበር የተመዘበረ የመንግስት ሀብትና ንብረት የማስመለስ ምጣኔ ወደ 87% ማሳደግ፣
- ልዩ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተፈፀሙ ወንጀሎች አስተዳደር ጥራት እና ውጤታማነት ማሳደግ
- የወንጀል ምርመራ ሥራ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት በመስራት ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፖሊስ የሚመለሱ መዝገቦች ወደ 1% ለመቀነስ እንዲሁም ምስክርና ማስረጃ በመጥፋት የሚቋረጡ የወንጀል ክስ መዝገቦች የመቋረጥ ምጣኔ ወደ 2.25% ለማድረስ ይሰራል፡፡
- ለዐቃቤ ህግ የሚቀርቡ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች የማጥራት ምጣኔን 100% ለማሳካት ይሰራል፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ከተሰጠባቸው መዝገቦች መካከል የማስቀጣት ምጣኔን በእቅድ 98.75% እንዲሁም በተከሳሽ 93% ለማድረስ በእቅድ ተይዞ አፈጻጸሙን 1ዐዐ% ማድረስ ተችሏል በ2ኛ አጋማሽም ይህንን ግብ ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፤
- ዐ/ህግ ይግባኝ በጠየቁባቸው መዝገቦች የፍርድ ቤት ውሳኔን እንዲሻር ወይም እንዲሻሻል የማድረግ ምጣኔ በመዝገብ ወደ 91.25% እና በተከሳሽ 93% እንዲሁም የሰበር በመዝገብ 91% እና በተከሳሽ 93% ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፤
- ተከሳሾች ይግባኝና ሰበር የጠየቁባቸው ጉዳዮች የፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲጸና ወይም እንዲሻሻል የማድረግ አቅም በመዝገብ 90% አፈጻጸም እንዲሁም በተከሳሽ 93% ማድረስ እንዲሁም ሰበር በመዝገብ ወደ 90.5% እና በተከሳሽ 91% እንዲርስ ይደረጋል፤
- በሴቶችና ህጻናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች የፍትሐብሔር የመርታት ምጣኔን ወደ 97% ከፍ ማድረግ፣
- የዐቃቤ ህግ የወንጀልና ፍትሐብሔር መዝገቦች ጥራትና ውጤታማነትን በህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ማረጋገጥ፣
- በናሙናነት በተመረጡ 58 የወንጀል 6 የፍትሐብሄር ጉዳይ መዛግብት ላይ የህግ ኦዲት ምርመራ የሚደረግ ሲሆን በተለያዩ የህግ ጉዳዮችና አሰራሮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በማጣራት 100% ምላሽ መስጠት፤
- መንግስት ከሳሽ በሆነባቸው የፍትሐብሔር መዝገቦች እንዲሁም ተከሳሽ በሆነባቸው የፍ/ሔር መዝገቦች የመርታት ምጣኔን አፈጻጸም ወደ 92% ለማሳካት የሚሰራ ሲሆን ለመንግስት ገቢ እንዲሆን በፍ/ቤት ከተወሰነው ሀብት ወደ 80% እንዲሁም ክስ ሳይመሰረት በድርድር የማስመለስ ምጣኔ ወደ 30% ለማሳካት በትኩረት ይሰራል፤
- ዐቃቤ ህግ ይግባኝ እና ሰበር የጠየቁባቸው የፍትሐብሔር መዝገቦች ውጤታማነት 94% እንዲሁም ተከሳሾች ይግባኝ እና ሰበር የሚጠይቁባቸው የፍትሐብሔር መዝገቦች የፍ/ቤት ውሳኔ እንዲጸና የማድረግ ምጣኔ 92% ለማሳካት ይሰራል
- የመንግስት የግዥ ውሎችን የህግ ቅርጽ የማስያዝና የማጽደቅ ስራ የሚሰራ ሲሆን ለሴክተር መ/ቤቶችና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በፍትሀብሄር ጉዳዮች 100% የህግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡
- የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማማከር ስራን ጥራትና ውጤታማነትን ማሳደግ፣
- ለወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶችን በህግ ጉዳይ የማማከር እና እንዲረቀቁና አስተያየት እንዲሰጥባቸው የሚቀርቡ አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች አጠናቆ የማቅረብ አቅም ወደ 100% የማሳደግ ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡
- በስራ ላይ ከሚገኙ ሕግጋት መካከል በ1 ህግ ላይ የክፍተት ዳሰሳ ጥናት በማድረግ ለአስፈጻሚ አካላት ለውሳኔ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
- የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ ግንዛቤ ማሳደግ
- በ2017 ሁለተኛ ግማሽ ዓመት ለሕ/ሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ወደ 18,000 የማሳደግ ስራ የሚሰራ ሲሆን 1100 የንቃተ ሕግ ማስተማሪያ ብሮሸር የማሰራጨት ስራም በትኩረት ይሰራል፤
- በ2016 በጀት ዓመት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና በፌደራል ደረጃ የወጡ ህጎችን በማሰባሰብ እና በማስጠረዝ ለአስፈጻሚ አካላት ተደራሽ የሚደረግ ሲሆን በተቋሙ ድህረ-ገጽ በመልቀቅ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋል፤
- ጠበቆች ለፍትህ ሥርዓቱ አጋዥነታቸው ማጠናከር
- የህግ ባለሙያዎች የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠኝ ጥያቄ በመቀበል መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙት የጥብቅና ፍቃድ እንዲሰጣቸው የማድረግ እና ፈቃዳቸውንም እስከ ሀምሌ 30/2017 ዓ.ም 100% እንዲያሳድሱ ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል፤
- በጠበቆች ላይ በሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ ምላሽ ወደ 100% እና በዲስፕሊን ጉባኤ ውሳኔ እንዲያገኙ ወደ 100% ለማሳደግ ይሰራል፤
- ጠበቆች የፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ኃይል ለማድረግ ከሙያቸውና ከሥራቸው ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ 1 ጊዜ ሥልጠና የመስጠት፣ በጥብቅና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ 3 ዙር ከፍ የማድረግ እና ጠበቆች ከፍትህ አካላት ጋር ባላቸው መስተጋብር ዙሪያ በየግማሽ ዓመቱ የውይይት መድረክ የማመቻቸት ስራ ይከናወናል፤
- ጠበቆችና ነጻ የህግ ድጋፍ ማዕከላት አቅም ለሌላቸው /የድህነት ማረጋገጫ ያቀረቡ/ ዜጎች ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ 100% ማመቻቸት፣
- የዜጎችን በሲቪል ማህበራት የመደራጀት መብታቸውን ማረጋገጥ፤
- የሲቪል ማህበር የፈቃድ ይሰጠኝ ጥያቄ በመቀበል መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙት የሰውነት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው የመከታተል እና ፈቃድ የወሰዱ ሲቪል ማህበራት በበጀት ዓመቱ ፈቃዳቸው እንዲያሳድሱ እንዲሁም ማህበራቱ ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጪ እንዳይቀሳቀሱ 3 ዙር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፡፡
- የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ውጤታማነትን ማሳደግ፣
- እንዲረጋገጡና እንዲመዘገቡ የቀረቡ ሰነዶችን ህጋዊነት በ30 ደቂቃ የማረጋገጥ አገልግሎት የመስጠት፣ የተረጋገጡና የተመዘገቡ ሰነዶች ሕጋዊነትና ትክክለኛነት 3 ዙር ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ እና በሠነድ ማረጋገጥ፡፡
- በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከልና ቁጥጥር ውጤታማነትን ማሳደግ
- በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን የግብረ-ኃይሉ አፈጻጸም በግማሽ ዓመቱ መገምገምና ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ሥራ በትኩረት ይሰራል፤
- በሰው መነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር መከላከል ዙሪያ 2 ጊዜ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ማመቻቸት እና ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ጥናት የማድረግ ሥራ ማከናወን፡፡
- የዜጎች ሰብአዊ መብት አጠባበቅ ውጤታማነት ማሳደግ፣
- የሰብዓዊ መብት ድርጊት-መርሃ ግብር የፈጻሚ አካላት ዕቅድና አፈጻጸም 2 ጊዜ የድጋፍና ክትትል ማድረግ እና በግማሽ ዓመቱ የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ማዘጋጀት ስራ ይከናወናል፤
- በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ዙሪያ ለፈጻሚዎች 1 ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና 2 ዙር የሕብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ማዘጋጀት፤
- የተጠርጣሪዎችን እና የታራሚዎች ሰብዓዊ መብት ለማስከበር በፖሊስ ማቆያ /ማረፊያ/ ቤት በየሳምንቱ እና ድንገተኛ ጉብኝት ማድረግ እንዲሁም በማረሚያ ቤቶች በየወሩ ጉብኝት የማድረግና ችግሮችን በቅርበት እንዲፈቱ ተገቢውን ትኩረት ይሰጣል፤
ዕሴቶች
- የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣
- ገለልተኝነት፣
- ታማኝነት፣ ግልፀኝነትና፣ ተጠያቂነት፣
- ቀልጣፋነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተደራሽነት እና ወጪ ቆጣቢነት፣
- እኩልነትና የአልጋይነት ስሜት፣
- ውጤትና ተገልጋይነት ተኮር መሆን፣
- የተቀናጀ የፍትህ አገልግሎት፣
- ለለውጥ ዝግጁነት፤
- ሰብዓዊነት፤
- ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት፤
- መረጃን ለልማት ማዋል
