የመስቃን ወረዳ ውሀ/ማ/ኢ/ ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
ዓላማ
በወረዳው በቂና አስተማማኝ የሆኑ ተቋማትን በመገንባት አሁን ያለው የወረዳው የውሀ ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎ ህ/ሰባችንን ሙሉ በሙሉ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ እንደሆነ ማድረግ የማዕድንና የኢነርጂ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም ለመስኖ የሚውሉ የውሀ ተቋማትን በመገንባት የከፍተኛ ልማትና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆነ ንቁና ጤናማ ህ/ሰብ እንዲኖር ማድረግ ፡
ተልዕኮ
ህ/ሰቡ ሌሎች የልማት ሀይሎችንና አጋሮችን በማስተባበር የውሀ የማዕድን ኢነርጂ ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎችናንና ፕሮግራሞችን መሰረት ያደረገና ተፈጻሚነት ያለው የልማቱ መረሀግብር በመቅረጽ የተቀናጀና ዘለቄታዊ የሆነ የውሀ ማዕድንና ኢነርጂ አስተዳደርን በማስፈንና የውሀ/ማ/ኢ/ ሀብታችን ለወረዳው አልፎም ለሀገራችን ህዘብ እድገትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና መጫወት በሚችል መልኩ እንዲለማ ማድረግ
የስራ ሂደቱ መጠሪያ የመጠጥ ውሀ ግንባታና ክትትል /ቅጥጥር
- የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት ክትትል ፣ግንባታና ቁጥጥር ማድረግ
- -የተሰራ ስራ ለክቶ ወስዶ ክፍያ ሰርትፍኬት መስጠት
- የመጠጥ ውሀ ግንባታ ክትትልና ቁጥጥር መስራት
- የምንጭ ማጎልበት የውሀ ማከፋፈያ ና የግንባታ ቁጥጥር ማድረግ
ንፁህ ውሀ መሳርያዎችና ጥገና ተቋማት አስተዳደርዋናስ/ሂደት
- -የእጅ ፓምፕ ጥናት ማድረግ
- የቧንቧ መስመር ጥገና ማድረግ
- የሮፕ ፓምፕ ስርጭት ማድረግ
- –በገጠር ንፁህ መጠጥ ውሀ በቀበሌ ደረጃ ፊደሬሽን ማደራጀት
- -የውሀ ተቋማት የኦዲት ስራ መስራት
- -ለማህበራትና ፌደሬሽን የአቅም ግንባታነ ስልጠና መስጠት
- አዲስ በተገነቡ ተቋማት ማህበር ማደራጀት
- የውሀ ተንከባካቢዎችና ኦፕሬተሮች ስልጠና መስጠት
- አዲስ ለተደራጁ ማህበራት እውቅና መስጠት
- ለአዲስ ተቋማት ቁጠባ ማስጀመር
የመስኖ ልማት ጥ/ዲ
- ለመስኖ ልማት የሚውሉ ወንዞች ጥናትና ዲዛይን ማድረግ
- ለመስኖ ልማት የሚሆኑ ቦታዎችን ጥናት ማድረግ
- -መካከለኛ ምንጭ ለመስኖ የሚሆኑ መለየት
- የሚሰሩ የመስኖ ልማቶች ቁጥጥር ማድረግ
- የመስኖ ልማት የወንዝ ጠለፋ ጥ/ዲ/ማንዋል ማዘጋጀት
የመዕድን/ሀ/ጥ/አስ
- ለማዕድን አምራች ማህበራት ቁጥጥር ማድረግ
- ለማዕድን አምራቾች ፍቃድ እንዲያድሱ ይደረጋል
- -በቀበሌ ህገ ወጥ የማዕድን አምራቾች ቁጥጥር ማድረግ
- የማዕድን አምራቾች ማህበራት ላይ የመረጃ ስርዓት መዘርጋት
- -የማዕድ አለኝታ ጥናት ማድረግ
- ማህበራት ለማዕድን አምራቾች የቴክኒክ ማድረግ
- አዲስ ለተደራጁ ማህበራት ለስራ አጥ ወጣቶች ፈቃድ መስጠት
የውሀ/ሀ/ጥ/አስ የስራ ሂደት
- በሁሉም ቀበሌዎች የውሀ መገኛ ቦታዎች ጥናት ማድረግድ
- የውሀ ተቋማት ህክምና መስጠት
- የውሀ ተቋማት ወቅታዊ መረጃ መሰብሰብ
- -የውሀ ተቋማቱ የመረጃ ስርዓት መርጋት
- ውሀ መገኛ ቦታዎችን ጥናት ማድረግ
በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose
ራዕይ
በውሀ ማዕድን /ኢ/ ሀብት በተቀናጀ መልክ በዘለቄታዊ ፍሀዊና በሆነ መንገድ ለምቶ ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊዕድገት ወሳኝ ድረሻ አበርክቶ ማየት
እሴት
የጽ/ቤቱ እራዕይ ፣ተልዕኮና የስልጣን ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን የሚከተሉትን እሴት መለያቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ ፡፡
- ህ/ሰቡን ያሳተፈ የውሀ ተቋማት መገንባት
- በጋራ ለጋራ ራዕይና ተልዕኮ መሰራት
- ለመልካም አስተዳደር መሰፈን የፀና እምነት መኖር
- የውሀ ተቋማትን መንከባከብና መጠቀም
- የውሀ ተቋማት በህ/ሰቡ እንዲተዳደሩ ኮሚቴዎችን ማብቃት
- ግልፀኝነት ፣ታማኝነትና ፣ተጠያቂነትን ማስፈን
