የመስቃን ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት

የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

photo 2025 06 25 06 12 01

የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

የመስቃን ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የአካባቢ ፀጥታና ሠላም የተረጋገጠበትና የህብረተሰቡ ደህንነት የተጠበቀበት ወረዳ ተፈጥሮ ማየት፣

ተልዕኮ

በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ብቃት ያለው የሚሊሻ ኃይል  በመመልመል፣ በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ በማሰማራት፣በማጥራትና የሎጅስቲክስ አስተዳደር በማካሄድ የሚሊሻ ኃይል ማፍራትና ተደራሽነቱን በማረጋገጥ የአካባቢ ፀጥታን ማስከበርና የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ፣.

አደራጅና ስምሪት ዋና የስራ ሂደት

በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ብቃት ያለው የሚሊሻ ኃይል  በመመልመል፣ በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ በማሰማራት፣ በማጥራትና የሎጅስቲክስ አስተዳደር በማካሄድ የሚሊሻ ኃይል ማፍራትና ተደራሽነቱን በማረጋገጥ የአካባቢ ፀጥታን ማስከበርና የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ፣

 

ምልመላና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት

  • ተልዕኮ

የዜጐች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ የህግ የበላይነትና የመልካም አስተዳደር፣ የህዝቡ ሰላም ፀጥታና ደህንነት የተረጋገጠበት ወረዳ ተፈጥሮ እና ለዚሁም ጉልህ ድርሻ የሚያበረክት ጽ/ቤት ሆኖ ማየት፡-

  • ራዕይ

አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን ዘመናዊ በማድረግ ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሣትፎ የሚታገዝና ብቃት ያለው የፀጥታ ኃይል በማፍራት ግጭቶችን በሃይማኖት ወይም በእምነት ሽፋን የሚፈፀም የአክራሪነትና የጽንፈኝነት አመለካከትን በብቃት በመለየትና በመከላከል የወረዳውን ፀጥታ፣ ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፡፡

  • ዓላማ፡-

የወረዳ ህብረተሰብ ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ የህግ የበላይነትና የዜጐችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በማስከበር፣ መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥና ለልማት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው፡፡

በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose

ዕሴት

ዕሴቶች የሴክተሩ ሠራተኞችና የሥራ አመራሩ የሚመሩባቸውና ወደፊትም በጋራ ሊከተሏቸው የሚገቡ የግልና የተቋም የአሰራር ፍልስፍናዎች ሲሆኑ ሴክተሩ፡-

  • ለህገ-መንግሥቱ ታማኝ መሆን፣
  • የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥ፣
  • ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣
  • የሕዝብ አገልጋይነት፣
  • ብዝኃነት መቀበልና ማክበር፣
  • ፍትሃዊነትና ሰብአዊነትን መላበስ፣
  • ራስን ማብቃት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ማወቅና መጠቀም፣
  • ሙያዊ ሥነ-ምግባር መላበስ፣
  • ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ትኩረት መስጠት እና
  • ኃላፊነትን መወጣት የሚሉት ናቸው፡፡