የመስቃን ወረዳ አመሰራረት

መስቃንና ማረኮ ወረዳ እንደ አንድ የአስተዳደር ወረዳ በ1950ዎቹ EC መጨረሻ – 1960ዎቹ EC መጀመሪያ (≈ 1958–1965 EC) መካከል ተመሥርቶ ነበር።የመስቃንና ማረኮ ወረዳ ስያሜ በማግኘት በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ለመሆን የቻለ ሲሆን በ2007 GC (1999/2000 EC) ሁለቱም እራሳቸውን ችለው የተለያየ ወረዳ  በመንግሥት መዝገቦች ሙሉ በሙሉ ታወቁ። መስቃን  ወረዳ 1999 EC እንደ አንድ የአስተዳደር ወረዳ  ስያሜ በማግኘት በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ መሆን ቻለ::

የወረዳችን አዋሳኞች

የመስቃን ወረዳ በስተሰሜን በኩል የሚያዋስነው የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሲሆን በደቡብ በኩል የስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ያዋስነዋል፡፡በስተምስራቅ አቅጣጫ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ሲያዋስነው በምዕራብ አቅጣጫ ደግሞ የሙሁርና አክሊል ወረዳ፤ስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮና ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡

የወረዳችን መገኛ አድራሻ

የመስቃን ወረዳ አስተዳደር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ስር ከሚተዳደሩት  4 ወረዳዎች እና 3 ከተማ አስተዳደሮች አንዱ ነው፡፡

መስቃን ወረዳ አስተዳደር በስሩ 26 የገጠር ቀበሌዎች እና 3 ከተሞች እንዲኖሩት ተደርጎ የተዋቀረ ሲሆን ወረዳው ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ 1550 ሜትር እስከ 3500 ሜትር ሲሆን ይህም የአየር ንብረቱ በአብዛኛው ወይና ደጋ እና ምቹ እንዲሆን አድርጎታል፡፡የወረዳው ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ሲታይ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ከፍታው እየጨመረ ይሄዳል፡፡ይህም በመሆኑ በስተምዕራብ አቅጣጫ የተዘረጋውን የዘቢዳር ሰንሰለታማ ተራራ እንዲጋራ አድርጎታል፡፡ወረዳው 10 ፐርሰንት ገደማ የሚሸፍነው ሰንሰለታማ ተራራ ሲሆን ይህም ተራራማና ሰንሰለታማ የሆነው የወረዳው ክፍል ዋና መገኛ በስተምዕራብ አቅጣጫ ከስልጤ ዞንና ከምዕራብ ጉራጌ ወረዳዎች የሚዋሰን ነው፡፡በአብዛኛው የወረዳው ክፍል የሚሸፍነው ሜዳማው የመሬት ክፍል ሲሆን  55 ፐርሰንት የሚሸፍነው የወረዳውን 35 ፐርሰንት የሚሸፍነው ደግሞ ተዳፋት የመሬት ክፍል ሲሆን በተራራማው የመሬት ክፍል በሜዳማው መካከል ተሰበጣጥሮ የሚገኝ የወረዳው የመሬት ክፍል ነው፡፡ ከወረዳው ፕላን ጽ/ቤት በተገኘው መረጃ መሰረት  በ2013 ዓ.ም ስታትስቲክስ ስሌት መሰረት የወረዳው የህዝብ ብዛት 206,261 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 107,256 (52 በመቶ)  የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 99,005 (48 በመቶ) የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡ አመታዊ የህዝብ ዕድገት መጠኑ 2.9 በመቶ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወረዳው ካለው አጠቃላይ ህዝብ በአምራች የዕድሜ (ከ15 እስከ 65) ደረጃ ያላቸው 54.6 በመቶ ሲሆን አምራች ባልሆነው የዕድሜ ክልል የሚገኙት (ከ15 አመት በታች እና ከ65 አመት በላይ) የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ደግሞ 45.4 በመቶ የሚሆኑት ናቸው፡፡ የህብረተሰቡ የአሰፋፈር ሁኔታ ሲታይ 84 በመቶ የሚሆነው በገጠሩ አካባቢ የሚኖር ሲሆን የተቀረው ከ16 በመቶ የሚሆነው የወረዳው ማህበረሰብ ደግሞ በከተማ ውስጥ የሚኖር ነው፡፡ የነዋሪው ህዝብ አሰፋፈር በአብዛኛው በወይና ደጋ እና በደጋማ አካባቢ በመሆኑ የህዝቡ የጥግግት መጠኑም 216 ሰዎች በኪሎ ሜትር ካሬ መሆኑ እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ይበልጥ ያንብቡclose
bu

በወረዳው እየተሰሩ ያሉ እና የተሰሩ ፕሮጀክቶቹ

533315249 1078561734465288 2872436615310856511 n
533191256 1078557744465687 7166601392203470455 n
520235828 1057698723218256 6995739731624748949 n
533225799 1078510117803783 8342703614328555827 n
533111283 1078561444465317 7262256271592804449 n
533141957 1078560947798700 4420549757666931211 n
521008992 1057698813218247 3072546231375134843 n

በመስቃን ወረዳ  የህዝቡ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት በካፒታል ፕሮጀክት በየደረጃው እየተሰሩ ያሉ ያላለቁና ጅምር ሥራዎችን በመኖራቸውን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በወረዳው ባሉ የተለያዩ ቀበሌዎች እየተሰሩ የሚገኙ የተለያዩ በካፒታል ፕሮጀችት የዋሉ የውሃ፤የድልድይ፤የጤና የመንገድ እንዲሁም በአዲስ መልክ እየተገነባ ያለው የመስቃን ወረዳ የአስተዳደር ህንጻ ግንባታ ስራ ና ሌሎችንም የልማት ስራዎች ይሰራሉ፡፡

በወረዳ የመንገድና ትራነስፖርት ጽ/ቤት በተገኘ መረጃ በወረዳ በመንግስት ፣ በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በባለሃብት ከሚገነቡ ድልድዮች መካከል የወሌንሾ2ኛ ቀበሌ የመኖ ድልድይ ግንባታ እና የግዴና አቦራት ቀበሌ በጎድኘ ወንዝ ምልከታው የተደረገባቸው ሲሆኑ እነዚህ ድልድዮች ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቆ ለትራንስፖርት ክፋት ማድረግ ተችሏል ።

በዚህም ለሁለቱ ድልድይ ግንባታው ወጪ የተደረገ ገንዘብ መጠን 7.7 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑንና እነዚህ ድልድዮች ባለመኖራቸው ለአመታት የህዝብ የመልካም አሰተዳደር ችግር ሆነው መቆየታቸው ይታውሳል።

ሆኖም አሁን ለአገልግሎት መዋል ከጀመሩ ጀምሮ በርካታ የአካባቢው ማህበረሰብ እፎይታን እንዳገኘና ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ማህበራዊ ፋይዳዎች እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም በመስራቅ ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተሠሩ የውሃ ፕሮጀክቶች በሴፍትኔት ካፒታል ፕሮጀክት 50ሺ ሊትር የሚይዝ ሪዘርቪየር 1. 5 ሚሊየን ግንባታው ተናቆ በንግስት ካፒታል በጀት ከ2 ሚሊየን በላይ ፓምፕ ቧንቧና መገጣጠሚያዎች ተገዝተው እየተገነባ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ግዴና አቦራት ቀበሌም እንዲሁ ሞሬ አካባቢ 50ሺ ሊትር የሚይዝ ሪዘርቪየር ጀነሬተር ቧንቧና መገጣጠሚያዎች ተገዝተው ሁለት ቦኖ ተገንብቶ ከ6ሚሊየን ብር በላይ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።

እንዲሁም በአፍሪካ ኢምፓወርመንት ሁለት ምንጮች ተገንብተው ከገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ብሎም በሰሜን ሸርሸራ ቀበሌ በበጎ አድራጎት ግለሰቦች 30ሺ ሊትር የሚይዝ ሪዘርቪየር 2.5ኪ/ሜ የተዘረጋበት ቧንቧና መገጣጠሚያ ሰርፌስ ፓምፕና ቦርድ እንዲሁም የስሪፌዝ ቆጣሪና መስመር ዝርጋታ ተሸፍኖ ስራወ በመጠናቅ ላይ እንደሚገኝ የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ገልጿል።

በየሲለና በጎ አድራጎት ድረጅት በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበለያት 16 ምንጮችና 6 የእጅ የውሃ ጉድጓድ ተቆፍረው ለአገልግሎት መዋላቸውንና በግራር ቤት ተሃድሶ ማህበር ጆሌ 1 ሚካኤሎናወሌንሾ1 ቀበሌ መለስተኛ ጥልቅ ጎድጓድ ተቆፍሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሆነ ተገልጿል።

በመንግስት አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታ ችግሮችን ከማህበረሰቡ ቅርብ ሆኖ ለመስራትና የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ የተጀመሩ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብና በጥራት ማጠናቀቅ ይቻላል፡፡

back