የቅርብ ጊዜ ዜናዎች
የጥንት መሪዎች የባህላዊ ንግስና መስጫ ቦታ ነበር በጥንት ዘመን የአንድ አካባቢ መሪዎች እንደየ አካባቢው ባህል እና ስርዓት መሰረት መሪዎች ሲሾሙ
Read More
create website meskan worda
መስቃንና ማረቆ ወረዳ እንደ አንድ የአስተዳደር ወረዳ በ1950ዎቹ EC መጨረሻ – 1960ዎቹ EC መጀመሪያ (≈ 1958–1965 EC) መካከል ተመሥርቶ ነበር።የመስቃንና ማረኮ ወረዳ ስያሜ በማግኘት በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ለመሆን የቻለ ሲሆን በ2007 GC (1999/2000 EC) ሁለቱም እራሳቸውን ችለው የተለያየ ወረዳ በመንግሥት መዝገቦች ሙሉ በሙሉ ታወቁ። መስቃን ወረዳ 1999 EC እንደ አንድ የአስተዳደር ወረዳ ስያሜ በማግኘት በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ለመሆን የቻለ ሲሆን የሚያዋስነው በስተሰሜን የደቡብ ሶዶ ወረዳ, በስተደቡብ የስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ,በስተምስራቅ አቅጣጫ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ሲያዋስነው በስተምዕራብ አቅጣጫ ደግሞ የሙሁርና አክሊል ወረዳ፤ስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮና ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳዎች ያዋስኑታል፡፡
የመስቃን ወረዳ እና የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና ከተማ መቀመጫ ቡታጅራ ሲሆን ከጉራጌ ዞን ውልቂጤ ከተማ 96 ኪ.ሜ ከክልላችን ርዕሰ መዲና ሆሳና 97.1 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኝ ሲሆን፤ ወረዳዋ 500 ኪ.ሜ ስኬር የቆዳ ስፋት ላይ ያላት እና በ26 የገጠር ቀበሌ በ4 ማዘጋጃ መዋቀር ችሎዋል፡፡
በዋናነት የሚመረቱት የግብርና ምርቶች ስንዴ፣ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ በርበሬ፣ ማሽላ፣ አተር እና ባቄላ ናቸው። በወረዳው ዋና ዋና የምግብ ሰብሎች በቆሎ እና ማሽላ ሲሆኑ ለገበያ የሚመረተው በርበሬ፣ስንዴ እና ጤፍ ናቸው።













ፏና ፏፏቴ:- ስያሜ ያወጡለት አባ ተወልደ ሚባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ በገትዬ ተራራና በግደቧር ተራሮች መሃል ይገኛል፡፡ የጀግኖች የእነ ዥርመከር፣ዳረጎት፣ተወልዶና የአስፎ መካነ መቃብሮች መገኛ ስፍራም ነው፡፡

የጎሎቦ ተክል ድንጋይ:- መስቃን ወረዳ ቀበሌ፣ምእራብ መስቃን የቦታው ልዩ ስም፣ ኢሎል ከቢዳራ ሜዳ ርቀት ፣2.5ኪሜ ከማእከል ቡታጂራ 12.5 ኪሜ ከቢዳራ ታዳጊ መዘጋጃ 3.5ኪሜ እድሜ ፣ 600አመታት በፊት

ቢዳራ ጠባ(ሜዳ):-17 ሄክታር ሜዳ ቦታ ሲሆን የፈረስ ጉግስ ውድድርና ልምምድ ማድረጊያ የነበረ ቦታ ነው፡፡ ቦታው ከየሰንጋውና ከየሞጣው (ከየክፍለህዝቡና ) ጀግኖች ለጦርነቶች ተመልምሎ ሚሰለጥኑበት ቦታ መሆኑን የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

የኢሎል:-ስል ሴራ ቦታ ማለትም የመስቃን ቤተጉራጌ ሴራዎች ደንቦች ማርቀቂያ ቦታ የሹመት ቦታ አዝማች አበጋዝ ኢቴ ጎሽቶ ገራድ ደማም የክብር ሹመት መስጫ ቦታ ሃገር በቀል ‹(ዝግባ በቁጥር 5) መገኛ ቦታ

የነሻዶ፣ ባዴ፣ ገራድ ባለከሽና ብዙ ጀግኖች መቃብር ስፍራ

የጥንት መሪዎች የባህላዊ ንግስና መስጫ ቦታ ነበር በጥንት ዘመን የአንድ አካባቢ መሪዎች እንደየ አካባቢው ባህል እና ስርዓት መሰረት መሪዎች ሲሾሙ
Read MoreWelcome to WordPress. This is your first post. Edit or delete it, then start writing!
Read More