ፏና ፏፏቴ

#ፏና የሚገኘው፦ “በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት – ምስራቅ ጉራጌ ዞን – መስቃን ወረዳ የተቦን ቀበሌ (ከብሻሸ አበቦት) በሚባል መንደር ነው።በሰንሰለታማው “ዘቢዳር ተራራ ፈርጥ” ስር የሚገኝ አስደናቂ ተፈጥሮ የተላበሰ ስፍራም ነው።ከቡታጅራ በግምት 15 ኪ.ሜ ዕርቀት ገደማ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ500 አመት በላይ ያስቆጠረና ከ13 ትውልድ በላይ የተፈራረቀበት ነው።#ፏና፦ የሚለው ስም የሰጡት አባ ተዎልደ ናቸው።#ፏና የገትዬ ተራራና የጊደርወ ተራራ በመሀል ሰንጥቆ እርንዛፍ ወንዝን ይቀላቀላል።# የፏና ፏፏቴ በዙርያው የከብሻሽን ተራራ ጨምሮ በርካታ ተራራዎችና ዙርያውን በትልልቅ ደኖች፣ ወንዞች የተከበበ ሲሆን፤ የእሪንዛፍ ወንዝ፣ ጊደቦር ምንጭ፣ የገትዬ ኒሻ ተራራ፣ የደማም አምባ ተራራ፣ የአመልማል ተራራ፣ የአበቦትና የበረገዝ ተራራዎች ለፋና ውብ የሆነ ገፅታን አላብሰውታል።#ፏና፦አባ ተዎልደም መራሮ ደርሰው ጥቅጥቅ ደን ተመለከቱ ጫካውንም ማየት በጀመሩ ጊዜ ትልቅ ዋሻን ያገኛሉ ወና ዋሻ/የነሀሱ ዋሻ ብለው ስም አወጡለት ።#ከዋሻው ፊትለፊት ደግሞ ፏፏቴውን ሲያዩ በተፈጥሮው በመገረም ፏና ብለው ሰየሙት፤ ከዛ ጊዜ ጀምሮ “ፏና ” የሚል ስያሜ አግኝቶ እስከ ዛሬ ድረስ በፋና ስም ይጠራል።#በፏና፦ ዙርያ የባህላዊ የንብ ቀፎ ከፏፏቴው ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በንብ ቀፎ በተጨማሪ ወይራ፣ ቀርከሀ፣ የተዎልዶ ዝግባ የእሪንዛፍ ወንዝ፣ የጊዴቦር ምንጭ፣ የፋና ጥቅጥቅ ደንና የኮብራን ኒሻ ለአብነት የተጠቀሱ ናቸው።#የንብ ማር ማምረቱ ሂደት የአካባቢው ነዋሪዎች በጉዳ ዳኝነት ወይም በባህላዊ ዳኝነት ህግ የተወሰነ ስለሆነ አንዱ የአንዱን ንብ አርቢው ቀፎውን እንደ ማይወሰድና ሌባም እንደሌለ የአባቢው ሽማግሌዎች ይናገራሉ።# ይህ ድንቅ ስፍራ= የአካባቢውና በዙሪያው ካሉ ተወላጆች በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በተደጋጋሚ ለጉብኝት ሲመላለሱ ይስተዋላል።# በዚህ አጋጣሚ በሀገራችን ካሉ ተፈጥሮ ውብ ፀጋ ካላበሰቻቸው አካባቢዎች የበለጠ እንደሆነና መንግስት ይህንን ስፍራ ልዩ ትኩረት ቢሰጠው ለሀገራችን ከፍተኛ ገቢና የውጭ ምንዛሬ ሊያስገኝ ይችላል።

ፏና ፏፏቴ

#ፏና የሚገኘው፦ “በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት – ምስራቅ ጉራጌ ዞን – መስቃን ወረዳ የተቦን ቀበሌ (ከብሻሸ አበቦት) በሚባል መንደር ነው።በሰንሰለታማው “ዘቢዳር ተራራ ፈርጥ” ስር የሚገኝ አስደናቂ ተፈጥሮ የተላበሰ ስፍራም ነው።ከቡታጅራ በግምት 15 ኪ.ሜ ዕርቀት ገደማ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከ500 አመት በላይ ያስቆጠረና ከ13 ትውልድ በላይ የተፈራረቀበት ነው።  
481977724 956965609958235 2623270285907616567 n (1)
472598835 575976068684262 96938264013371567 n
472676625 575976085350927 5390633412663230892 n
472759575 575976118684257 1992398242001496055 n