የመስቃን ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
አቶ ጀማል በድሩ
የመስቃን ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ
ተልዕኮ
ወረዳዊ፣በዞናዊ፣ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡን ለሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያነሳሳ፣የሚያጎለብት፣ ተጠቃሚ የሚያደርግ የኮሙዩኑኬሽን ሥርዓት በመዘርጋት ተአማኒ፣ ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡
ራዕይ
የወረዳችን ህዝቦች በላቀ መረጃ በልጽገው የጋራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ተረጋግጦ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት ተጠናክሮ ማየት፣
ዓላማ
በወረዳዉ የሚዲያ ብዝሃነትና ተደራሽነት በማሳደግ፤ ዘመናዊና ውጤታማ የኮሚዩኒኬሽን አሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ሕብረተሰቡን የኢንፎርሜሽን ተጠቃሚ በማድረግ አንድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት ነው፡፡
እሴቶች
- ስራዎች የጋራ አመለካከትን ከመፍጠር ይጀምራሉ
- በእቅድ እንመራለን
- ፍታዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው
- በማያቆራርጥ ለውጥና በመሻሻል እናምናለን
- ጊዜና የሰው ሀይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶቻችን ናቸው
- ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን
- መረጃን ለልማት እናውላለን
- ውጤት ያሸልማል
- ተገልጋዮቻችንን የህልውናችን መሰረት ናቸው
- የሚዲያ ተከታዮቻችን መካሪዎቻችን ናቸው
- የሴቶችን፣የወጣቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን፡፡
- ዋና ዳይሬክቶሬት
- የኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን
- የሚዲያ ሞኒተሪንግና ጥናትና ምርምር ቡድን
- የመንግስት መረጃ ማእከልና የዲጂታል ሚዲያ አስተዳደር ቡድን
-
አገልግሎቶች
- የልዩ ልዩ ህትመቶች ዝግጅትና ሥርጭት አገልግሎት፣
- መንግስትንና ህዝብን የማገናኘት አገልግሎት፣
- መንግስትን ከሚዲያ የማገናኘት አገልግሎት፣
- የሚዲያ ሞኒተሪነግና የህዝብ አስተያየት ጥናት አገልግሎት
- የህዝብ አመለካከት ጥናት የማድረግ አገልግሎት
- የተቋም አላማና ፖሊሲ ላይ የጥናትና ምርምር የማድረግ አገልግሎት
- መረጃ የማከማቸት፣ የማደራጀት እና የማቅረብ አገልግሎት፣
የተለያዩ መረጃዎችን የመልቀቅ አገልግሎት፣
