የመስቃን ወረዳ ሴቶችናህጻናት ጽ/ቤት

የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

photo 2025 06 25 06 14 20

ዓላማ

  • ሴቶች በህ/ሰብ ውስጥ በማንኛውም መስክ ሰብአዊና የንብረት ባለቤትነትና ተቆጣጣሪነት መብታቸው እንዲከበርና እኩልነታቸው እንዲረጋገጥ በኢኮኖሚ፣በማህበራዊና በፖለቲካዊ ተሳታፊ፣ተጠቃሚና ውሳኔ ሰጭ እንዲሆኑ ማስቻል፡፡
  • ህፃናት መብቶቻቸው እንዲከበርና ደህንነታቸው እንዲረጋገጥ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ከህገ ወጥ የህፃናት ዝውውር ከሀይል ጥቃት እንዲጠበቁ ፣አምራችና ሀገር ተረካቢ ዜጎች እንዲሆኑ ማስቻል፡፡
  • የሴቶችና የህፃናት አደረጃጀት ብቃታቸውን አሳድገው ሚናቸውን እንዲወጡ ማስቻል፡፡

ተልዕኮ

የሴቶችን በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ የህፃናትን መብትና ደህንነት ማስጠበቅና የፆታ ዕኩልነትን ማስፈን፡፡ለዚህም ተፈፃሚነት፡-

  • የግንዛቤና ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ መፍጠር፣
  • ሴቶች እና ህፃናት እንዲደራጁ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ማብቃት፣
  • በህጎች ፖሊሲዎችና የልማት ፕሮግራሞች የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ መካተቱንና መፈፀሙን ማረጋገጥ፤ ማስተባበር፣ ክትትል ማድረግና ድጋፍ መስጠት፣
  • የሴቶች ልዩ ድጋፍ እርምጃዎች አፈፃፀም እና ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት ቦታ መመደባቸውን ማረጋገጥ
  • የህጻናትና ሴቶችን ስብዕና መገንባት
  • የሴቶችና ህፃናት ሰብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ማስተባበር
  • በቤተስብ ደረጃ . . .የሴቶችን ውሳኔ ስጪነት ብቃት ማጎልበት
  • የሴቶች አመራሮችን ጥምረት ማጠናከር
  • የሴቶች አመራርነትን አቅም በማሳደግ ብቁ ማድረግ
  • የተጠያቂነት ማዕቀፍ ማጠናከር

ይበልጥ ያንብቡClose

ራዕይ

“በ2022 ሴቶች በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና በባህል መስኮች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት፤ የህፃናት መብትና ደህንነት የተከበረባት፤ የህፃናት መልካም ስብዕና የጎለበተባት እና የስርአተ-ጾታ እኩልነት የሰፈነባት ወረዳ ማድረግ”፡፡

እሴት

  • አሳታፊነትና ፍትሃዊነት
  • ግልጽነትና ተጠያቂነት
  • ፈጠራ
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት
  • የአገልግሎት ጥራት
  • የቡድን ስራ

የሴቶች ዘርፍ፡-

በበጀት አመቱ በወረዳችን የሚፈፀሙ የተለያዩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የሀይል ጥቃቶች ለመከላከልና ለማስወገድ በተሰራው የግንዛቤ ሥራ የህብረተሰብ ክፍሎችን ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል ይሁን እንጂ በዚህ ተግባር የህብረተሰብ ክፍሎችን ማሳተፍ የተቻለ ቢሆንም በዞናችን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የሀይል ጥቃቶች የመጥፋት አዝማሚያ አሳይተው የነበረ ቢመስልም በአሁኑ ጊዜ በህሪያቸውንና ወሰናቸውን በማስፋት በአዲስ መልክ እያገረሹ በመሆኑ በዚህ በጀት አመት በትኩረት የሚሰራበት ይሆናል፡፡

ህጻናት ዘርፍ

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት ድጋፍና ክብካቤ ማሳደግ

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ህፃናትን የድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት ለማጠናከር የማህበረሰብ አቀፍ፣ የማዋሀድና ማቀላቀል፣ የአደራ ቤተሰብ፣ የጉዲፈቻና የህፃናት ማሳደጊያ አገልግሎት ፕሮግራሞች ተቀርጸው ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን በእነዚህ አማራጭ የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ ፕሮግራሞች ህፃናት ተጠቃሚ አንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በህፃናት ድጋፍ፣ እንክብካቤ እና ጥበቃ አንጻር በገጠርና በከተማ ቤተሰብን ለማጠናከር የሚያስችሉ የምግብ ዋስትናና የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ የማድረግ ተግባራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በመሰራቱ  ቀድሞ ይታይ የነበረውን ጉድለቶችን በመቅረፍ በኩል መሻሻል የታየበት ቢሆንም ከተደራሽነት አንጻር የታየው ክፍተት በተፈለገው ደረጃና መጠን ተፈጻሚ እንዳይሆን ያስቻለ ስለሆነ  በቀጣዩ የስራ ዘመን መምሪያው በየደረጃው ያለውን መዋቅር በማጠናከርና ተግዳራቶችን ለይቶ በመቅረፍ ውጤታማነት ማስፈን የሚያስችል ጠንካራ ስራዎችን የሚተገብር ይሆናል፡፡

ህጻናት አደረጃጀቶችን አቅም ማሳደግ፤

የህጻናት ተሳትፎን ለማሳደግ ወጥነት ያለው የህፃናት ፓርላማዎች የሚቋቋሙበትና የሚመሩበት የአሰራር ማዕቀፍ/የህፃናት ፓርላማ ጋይድላይን መሰረት በማድረግ በጀት አመቱ 1 ጊዜ  በወረዳ ደረጃ የህፃናት ፓርላማ በማቋቋምና   በዚህም ለህጻናት አደረጃጀቶች ስልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ እንዲጠናከሩ በማድረግ እንዲሁም የህጻናት ክበባትን በማጠናከርና አዳዲስ የህፃናት ክበባት በማቋቋም  የህጻናቱን ተሳትፎ በመሳደግ አበረታች ውጤት ተገኝቶበታል፡፡

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ በማካተት ተቋማዊነት ማሳደግ

በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ተቋማት የሴቶችን ጉዳይ በሁሉም ዘርፍ እንዲያካትቱና ብሎም ተቋማዊ እንዲያደርጉ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅማቸውን ለማጎልበት ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የአመለካከት ለውጥ፣ ሴቶችን የማብቃት፣ የአሰራር ስርአት የመዘርጋት፣ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች፣ የተጠያቂነት ስርዓት የመዘርጋት፣ ተቋማዊነት የማጎልበት፣ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የመተንተንና የመሰነድ ስራዎች መስራት፡፡

በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose