የመስቃን ወረዳ ሰራተኛናማህበራዊ ጽ/ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
አቶ ተሾመ
የመስቃን ወረዳ ሰራተኛናማህበራዊ ጽ/ቤት ሀላፊ
ራዕይ
በ2022 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሠላም ያሰፈነበት ፣የሥራ ዕድሎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የማኀበራዊ ደኀንነትና ልማት አገልግሎት ተስፋፋቶ ማየት
ተልዕኮ
የሥራ ስምሪት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የኢንዱስትሪ ሠላም እንዲሰፍን፡ የሠራተኛውን ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የሥራ አከባቢዎችን እንዲሻሻልና የዜጐችን ማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት(የአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ፣ አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙና ተሳትፎአቸው እንዲጐለብት፣በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በድህነት፣ተጋላጭናመገለል ውስጥ ለሚገኙ ዜጐች የተለያዩ ድጋፎች) እንዲያገኙ ማድረግ የሚሉት የሴክተሩ ተልዕኮዎች እንዲያገኙ ማድረግ የሚሉትን የሴክተሩ ተልዕኮዎች ናቸው፡፡
ዕሴቶች
- ታማኝነት
- ግልጽነትና ተጠያዊነት
- ፍትሀዊነትና እኩልነት
- አሳታፊነት
- ቀጣይነት ያለው መሻሻል
- በዕውቀት መምራት/መስራት
- ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት
- ውጤታማነት
በማህበራዊ ደህንነት ጥበቃ ዋና ስራ ሂደት
- ማህበራዊ ጥበቃ ኮሚቴዎችን መደገፍና ማጠናከር
- ከህዝብና ከመንግስት ጋር በመተባበር ተጋላጮች ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ እቅድ
- በራስ አቅም ሃብት ለማሰባሰብ የሚረዳ ፕሮፖዛል በመቅርጽ በፋይናንስ እንዲደገፉ ማድረግ
- አካል ጉዳተኞችን በጉዳት አይነትና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ።
- አረጋዊያንን መለየትና መመዝገብ
- የስጋ ደዌ ህሙማንን መለየትና መመዝገብ ማህበር እንዲመሰረት ማድረግ
- የአረጋዊያን ማህበር ማጠናክርና መደገፍ
- የአካል ጉዳተኛ ማህበር ማጠናከርና ድጋፍ ማድረግ ።
- ለአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
- የአካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ።
- ለአካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ።
- አካል ጉዳተኞች የጥገና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ።
- አካል ጉዳተኞች የፊዚዮ ትራፒ አገለግሎት እንዲያገኙ ማድረግ።
- ለአይነ ስውራን የብሬል አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ።
- ለአይነ ስውራን የቀይ በትር ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ።
- ለምኖ አዳሪዎች የማህበራዊና የስነ ልቦና ጋይዳንስ ምክር አገልግሎት መስጠት
- ለአካል ጉዳተኞች የተለያዩ የስነ ልቦና ድጋፍ ማቋቋምና የምክር አገልግሎት መስጠት ።
- የማህበራዊ ደህንነት ችግሮችን ለመከላከል ብሮሸሮችን አሳትሞ በማሰራጨት የህ/ሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ
- ልዩ ልዩ መድረኮችንና ስልቶችን በመጠቀም የህ/ሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ተጋላጭ የሆኑ የህ/ሰብ ክፍሎችን በማ/ሰቡ ውስጥ ተገቢው ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ (ከድጋፍና እንክብካቤ ጥምረቶች ጋር በመተባበር)
- በማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ አካል ጉዳተኞች፣አረጋዊያን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጮች አስፈላጊውን የማህበራዊ ድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እንዲያገኙ የተለያዩ አለም አቀፍ በዓላትና መድረኮችን በመጠቀም የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ለተለያዩ የህሰ/ብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር በአዲስና በፈረሱ ቀበሌዎች የማ/ሰብ አቀፍ ድጋፍና ጥምረቶች እንዲቋቋሙ ማድረግ ።
- አዲስ የአካል ጉዳተኛ ማህበር እንዲቋቋም ድጋፍ ማድረግና ነባር የአካል ጉዳተኞች ማህበር እንዲጠናከር ማድረግ ።
- የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲዎችን ተፈጻሚ ለማድረግ እንዲቻል የጥናት ስራዎ ች፣ የድርጊት መርሃ ግብሮች፣ የማስፈጸሚያ ሰነዶችና ማንዋሎችን ማዘጋጀት ።
- የአካል ጉዳተኞች የአረጋዊያን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ የህ/ሰብ ክፍሎች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ተግባራትን በመደበኛ እቅዳቸው አካቶ (main streaming) ስራ እንዲሰራና የእቅዳቸው አካል በማድረግ እንዲያከናውኑ ተገቢውን የማስተባበር፣የማቃናጀትና ስለአፈጻጸማቸው ወቅታዊ ግ/መልስ መስጠት ።
ስራ ስምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዋና ስራ ሂደት
- የስራ ገበያ መረጃዎችን ከመረጃ አመንጭ ተቋማት ማሰባሰብና ማጠናከር
- በሲቪል ሰርቪስ መ/ቤቶች በስራ ላይ የተሰማራ የሰው ኃይል መረጃ እንዲደራጅ ማድረግ
- በስራ ላይ የተሰማራ የሰው ኃይል መረጃ እንድደራጅ ማድረግ ።
- ክፍት የስራ ቦታ መመዝገብ።
- በወቅታዊ ስራ ላይ እድል ያገኙ ዜጎች መረጃ መሰብሰብ ።
- ህጋዊ የውጭ ሃገር ስራ ስምሪትና ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በተመለከተ አስተማሪ የሆኑ የህትመት ውጤቶችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት
- የሚድያ ተቋማትን በመጠቀም ስለ ውጭ ሃገርስራ ስምሪትና ስለ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት አስተማሪ የሆኑ ት/ታዊ መልዕክቶችን ማስተላለፍ
- የማ/ሰብ ውይይት የአፈጻጸም ግምገማና የማነቃቂያ ልምድ ልውውጥ መፍጠር
- ከስደት ተመላሽ ዜጎችን አቀባበል ማድረግና የተመላሾችን መረጃ ማደራጀት
- ከስደት ተመላሾችን መመዝገብና የአገልግሎት ፍላጎታቸውን በመለየት ድጋፍ እንዲያገኙ ማስተባበር
ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዋና ስራ ሂደት
- ቅንጅታዊ የትብብር መድረኮችን በመፍጠር የህ/ሰቡን ተሳትፎ የማሳደግ ተግባራት መፈጸም
- በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችንና የስራ ክርክሮችን እንዳይከሰቱ በልማት ድርጅቶች ውስጥ መከላከል
- በደርጅቶች የስራ ቦታ ትብብርና ማህበራዊ ምክክር አገልግሎት ስርዓት እንዲዘረጉ ድጋፍ መስጠት
- የ2ዮሽ የምክክር ስርዓት ለዘረጉ ድርጅቶች ድጋፍ መስጠት
- ለአስማሚየሚቀርቡ የወል ስራ ክርክር አቤቱታዎች በሙሉ ማስተናገድ
- ለአስማሚ ከቀረቡ አቤቱታዎች በስምምነት ያለቁ የወል ስራ ክርክሮች
- ከኢንዱስትሪ ሰላም መናጋት ጋር የሚገናኙና በአሰሪዎች፣ሰራተኞችና በመንግስት ተሳትፎ በ3ዮሽ የተፈቱ ጉዳዮች
- የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል በተለያዩ ድርጅቶች ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ
- በድርጅቶች ነባር በተቋቋሙ ጥምር የሙያ ደህንነትና ጤንነት ተከታታይ ኮሚቴዎችን ማጠናከርና ድጋፍ መስጠት
- በድርጅቶች ኤች:አይ ቪ ኤድስ ተከላካይ ኮሚቴዎችን ማቋቋም
- ኤች አይ ቪ ኤድስ ተከላካይ ኮሚቴ በተቋቋመባቸው ድርጅቶች ማጠናከርና ድጋፍ መስጠት
የማህበራዊ ችግሮች መከላከል ዋና ስራ ሂደት
- ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የኆኑ የሆኑ የህ/ሰብ ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ነባር የማህበረሰብ ድጋፍና እንክብካቤ ጥምረቶች ክፍሎ
- ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህሰብ ክፍሎች ን ድጋፍና እንክብካቤ ማሳደግ
- የማህበራዊ ችግሮችን ለመቀነስ የማህበራዊ ጥበቃ አስተባባሪኮሚቴና ቴክኒክ ኮሚቴ ማጠናከር
- የአረጋዊን መብት ለማረጋገጥና ድጋፍና እንክብካቤ ለማሳደግ በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራት ወይም ጥምረቶች የተደረገ ድጋፍ
- ነባር የአረጋዊያን ማህበርን ማጠናከር
- የማህበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ የአረጋዊያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ
- አረጋዊያንን ከጥቃት ለመከላከል ግንዛቤ መፍጠር
