Projects

የመስቃን ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት

የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

515485205 1047450184243110 8826763822827442542 n

አቶ ሙህዲን ኡስማን

የመስቃን ወረዳ የመንገድና ትራንሰፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ

ዓላማ

የትራንስፖርት እና የመንገድ ልማት አገልግሎት የሕብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጐት ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ፣ደህንነቱ የተጠበቀና ምቾት ያለው፣ ቀልጣፋ፣ ብቁ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጡ የተመጣጠነ በማድረግ ወረዳዊና በአዋሳኝ ወረዶች የትራንስፖርት አገልግሎት መስመሮች እንዲዘረጉ እና እንዲደራጁ በማቀናጀትና ትራንስፖርቱ በማንኛውም ረገድ እንዲያድግ በማበረታታት ነዉ፡፡፣ የሕዝብና የዕቃ መጓጓዣ ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ ነዉ፡፡

ተልኮ

ለወረዳው ሕብረተሰብ የተቀናጀ ልማት ለማምጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መንገዶችን በመገንባትና በማስገንባት እንደዚሁም በማስጠገንና በማስተዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋምነት በማስፋፋትና በማጠናከር እንዲሁም የህብረተሰቡ የመንገድ አጠቃቀምንና የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ በማሳደግ የትራንስፖርት ተጠቃሚነትና ደህንነትን እውን በማድረግና መላውን ህብረተሰብ በማደራጀትና በማነቃነቅ የሴክተሩ ዕቅድ ዝግጅት፤አፈጻጸምና ውጤት ላይ ማሳተፍ መቻል፡፡

አዳሪና /አዲስ የቀ/// እንዲካሄድ ማድግ

  • የቀ/// ለመጀመር ፕሮጀክቶች መለየት
  • የሶሺኦ ኢኮኖሚ ጥናት ማካሄድና መረጃዎች ማሰባሰብና የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
  • ስራውን በስታንዳርዱ መሰርት መሰራቱን መቆጣጠርና መከታተል

በመንገድ ግንባታው የህ/ ተሳትፎና የተለያዩ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ለማረጋገጥ በፕሮግራም መሰረት ሰፊ የህ/ ንቅናቄ ማድረግ

  • የህዝብ ተሳትፎና ንቅናቄ በመፍጠር የግንዛቤ ትምህርት መስጠት
  • ቅንጅታዊ ስራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተሞክሮች መቀመርና ማስፋፋት
  • ከባለድርሻ አካላት ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ማድረግ እና ስራዎችን በቅንጅት መስራት
  • የህብረተሰቡ ተሳትፎና ንቅናቄ ስራ የሴቶችና የወጣቶች ድርሻ በገንዘብ፤በእውቀት መለየትና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ
  • የተለያዩ በአካባቢ ባለሀብቶች የሚገነቡና የሚጠገኑ መንገዶች መለየት
  • በየመንገድ ዳር የችግኝ ተከለላ ማካሄድ

ቀላልና ወጪ ቆጣቢና ሌበርቤዝ የቀበሌ መንገድ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ላይ ክትትል ማድረግ

  • የቀ/// የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች በመቀበል ለሚመለከተው አካል ማውረድና መከታተል 

በፕሮግራሙ የሚፈጠረው የስራ እድል በአግባቡ መለየትና መመዝገብ

  • በፕሮግራሙ የሚሳተፍ የህ/ ክፍሎች በተገቢው መለየትና ማሳተፍ

የቀ//// መረጃና የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ማሰባሰብና ማደራጀት እንዲሁም ለሚመለከተው አካል ማተላለፍ

  • የቀ//// መረጃና የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ከባለሙያዎች ማሰባሰብና ማደራጀት እንዲሁም ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ

የስራ ሂደቱን እንቅስቃሴ አተገባበር በተመለከተ የተሟላ አገልግሎት መስጠትና ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ብሮሸሮች ማዘጋጀትና ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋፋት

  • በየዘርፉ የሚነሱ ቅሪታዎች ማጣራትና ምላሽ መስጠት
  • የተለያዩ ይዘት ያላቸው ብሮሸሮች ማዘጋጀት
  • የተዘጋጁ ብሮሸሮች አባዝቶ ማሰራጨት
  • በወረዳው ሚኒ ሚዲያ ስለመንገድ አያያዝና ትምህርት እንዲተላለፍ ማድ

በዳሬክቶሬቱ የሚሰቱጡ ዝርዝር ግቦች ይመልከቱClose

ራዕይ

የወረዳው ሕብረተሰብ ወደ አኮኖሚያ፤ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ማዕከላትና አገልግሎት ተቋማት የሚያደርስ በቂ፤ምቹና አስተማማኝ የመንገድ አውታር ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት ነው፡፡

ዕሴቶች

  • አሳታፊነትና ፍትሃዊነት፣
  • ግልጽኝነትና ተጠያቂነት፣
  • ፈጠራ፣
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣
  • የአገልግሎት ጥራት፣
  • የቡድን ስራ፣