የመስቃንወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ መልዕክት

Click edit button to change this text. Lorem ipsum dolor sit amet, adipiscing elit.

db

አቶ ደበበ ሰይፉ
የመስቃንወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ

ራዕይ

በ2017 የባህል ቱሪዝምና  ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የወረዳው ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ማድረግ፣

ተልዕኮ

ወረዳው በዋናነት የሚገኙ የህብረተሰብ ባህላዊ እሴቶች፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን/ቅርሶችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማትና በማስተዋወቅ፤ የህብረተሰቡን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓታችንን በማዘመን ወረዳችን ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም በህብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በላቀ ደረጃ በማሳደግ እና መልካም ገጽታ በመገንባት የወረዳችንና ብሎም የአገራችንን ዘላቂ የሆነ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ብልፅግና ማረጋገጥ፡፡

እሴቶች

  • ብዝሀነትን ማክበር
  • እንግዳ ተቀባይነት
  • ግልጽነት
  • ተጠያቂነት
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • የላቀ አገልግሎት
  • አሳታፊነት
  • ህዝባዊነት
  • ፈጠራን ማበረታታት
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት
  • የአገልግሎት ጥራት
  • በቡድን መስራት
  • መፍር መፍጠን

1.የባህል ታሪክ ቅርስ ጥናትና ልማት ዋና ስራ ሂደት

 የማንነት መገለጫ የሆነውን ባህልና ታሪክ የጋራ እሴቶቻቸውን በማጎልበት ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ባህልን ለማዳበርና ሀገረሰባዊ ዕውቀቶችን በማስፋፋት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማስቻል፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በማስቀረትና የባህል ወረራን በመከላከል የብሔሮችንና የብሔረሰቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ግብ ነው፡፡

 2.በቋንቋ ና ስነፅሁፍ ልማት ዋና ስራ ሂደት 

በወረዳው የሚገኘው የጉራጊኛ ቋንቋ ተጠንቶ ለምቶና ከመጥፋት አደጋ ተጠብቆ የሥራ፣የትምህርትና የብዙሃን መገናኛ ሆኖ መቀጠልና አጠቃላይ የስራ ቋንቋ መሆን እንዳለበትና አመላካች ጉዳዮች መሰራት፡፡የባህል እንዱስትሪ የወረዳው ብሄረሰብ መለያና መገለጫ የሆነውን እደጥበባት፣ ሥነ-ጥበባት እና ስነጽሑፍ በመፍጠር፣ በማዘጋጀት፣ በመስራትና  ለመድረክ በማቅረብ ባህሪያቸውን ፣ባህላዊ ፋይዳቸውንና ይዘታቸውን ጠብቆ  ከባህል ብረዛና ወረራ በመከላከል ለሥራ ዕድል ፈጠራና መልካም ገጽታን በመገንባት ለወረዳችንና ለሀገራችን  ልማትና ብልጸግና ለማዋል የሚያስችል ግብ መስራት ነዉ፡፡

   3.የቱሪዝም መስህብ ጥናት ጣበቃና ልማት ዋና ስራ ሂደት

  • በወረዳዉ የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶች በመጠበቅ፣ በማልማትና በማስተዋወቅ የወረዳዉን መልካም ገፅታ መገንባት ነዉ፡፡
  • የሀገር ዉስጥ ቱሪዝምን ለማስፋፋት በት/ቤቶችና በየመ/መስሪያ ቤቶች የሀገርህን እወቅ ክበቦችን በማቋቋም ማህበረሰቡ የአካባቢዉን ሀብት እንዲያወቅ በማድረግ የሀገር ዉስጥ ቱሪዝምን ለማሰፋፋት የተጣለ ግብ ነዉ፡፡
  1. የዘርፉ ገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዋና ስራ ሂደት
  2. በወረዳው የሚገኙ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቁጥር አነስተኛ፣ በስርጭት ውስን እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃቸው ዝቅተኛና ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም ብዛታቸውእንዲጨምር፣ ሥርጭታቸው እንዲሰፋና የሚሰጡት አገልግሎት እንዲሻሻል ለማድረግ የተጣለ ግብ ነው፡፡ወረዳዉ ያለውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብቶች በመጠበቅና በማልማት ልዩና ተመራጭ እንዲሁም ምቹ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች በማድረግ የጎብኚዎችን እርካታና የቆይታ ጊዜ በማሳደግና የጎቢኚዎች ቁጥር እንዲጨምር በማድረግ የዘርፉን ገቢ ማሳደግ አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ግብ ነው ፡፡

 

consequat. Duis aute irure dolor in reprehenderit in voluptate velit esse cillum dolore eu fugiat nulla pariatur. Excepteur sint occaecat cupidatat non proident, sunt in culpa qui officia deserunt mollit anim id est laborum.

በዳይሬክቶሬቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችClose