የጥንት መሪዎች የባህላዊ ንግስና መስጫ ቦታ ነበር

በጥንት ዘመን የአንድ አካባቢ መሪዎች እንደየ አካባቢው ባህል እና ስርዓት መሰረት መሪዎች ሲሾሙ ኃላፊነት ሲቀበሉ በተለያዩ ባህላዊ ስርዓት ንግስና እና ኃላፊነት ይቀበላሉ።

ከባህላዊ ስርዓቶች ውስጥ ደግሞ እንደየ አካባቢው ባህል እና ስርአት መሰረት ንግስና የሚሰጥበት እንዲሁም ባህላዊ ስርዓቱ የሚከወንበት የሚከናወንባቸው ቦታዎች አሉ።

በመስቃን ማህበረሰብ ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ህብረተሰቡን እና አገሩን የሚመሩ መሪዎች ንግስና የሚሰጥበት እና የሚጸድቅበት ቦታ ነበረው።

ይህም ቦታ በአሁኑ ወቅት የመስቃን ወረዳ ምዕራብ መስቃን ቀበሌ ውስጥ የዘቢደር ተራራ ግርጌ ላይ በሚገኝ ኢሎል ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው።

ኢሎል ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚካሄድ ባህላዊ የሹመት ስርዓት የአካባቢው መሪዎች ንግስናቸው ህዝብ በተሰበሰቡበት ይከናወን ነበር ።

ttt

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *