ህገ_ወጥነት በጋራ መከላከል እንደሚገባ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እና የመስቃን ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።
ሚያዚያ_ 28/2018 (የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን)
#ህገ_ወጥነት በጋራ መከላከል እንደሚገባ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እና የመስቃን ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እና የመስቃን ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት የጋራ ግብረ ሃይል በመስቃን ወረዳ የጆሌ ቆጬ ታዳጊ ማዘጋጃ ምልከታ ለማድረግ በወጣበት ወቅት ከማዘጋጃው ወጣ ብሎ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ቤት 210 ሊትር ቤንዚል እና 50 ባለ 30 ሊትር ለማጠራቀሚያነት የተዘጋጀ ጄርካን መውረሱን አስታውቋል።
የንግዱ ማህበረሰብ በዘፈቀደ የሚያደርው የዋጋ ጭማሪ ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል ለማድረግ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራረር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለፀው የጋራ ግብረሃይሉ ህገወጥነትን በጋራ መከላከል እንደሚገባ አፅንዎት ሰጥቷል።
በመጨረሻም የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ባለሙያዎች፣ የመስቃን ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ባለሙያዎች እና የመስቃን ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት የፖሊስ አባላት የጋራ ግብረ ሃይሉ አካል ሆነው በቅንጅት ሲሰሩ እንደነበር በመጥቀስ ህገወጦች ሲያገኝ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጠይቀዋል።
==================
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!
