ኢሎል
ኢሎል ለአስተዳደራዊ ምቹነት በባህላዊ መንገድ ሹመት የሚሰጥበት ስፍራ ነው።
መገኛውም በመስቃን ወረዳ ምዕራብ መስቃን ቀበሌ ውስጥ ከዘቢደር ተራራ ስር የሚገኝ እጅግ ውብ የሆነ በተፈጥሮ እና አገር በቀል እጽዋት የለመለመ ጥንት የተዘጋጁ በድንጋይ የተመቻቹ መቀመጫዎች ያሉት ስፍራ ነው ፡፡
ኢሎል በጥንት መስቃን ለአስተዳደር የሚመረጥ የተመረጠ ሰው ሹመት የሚጸድቅመት ቦታ ነው ፡፡
በኢሎል ለአስተዳደርነት የሚመረጠው ሰው ለመለየት የጎሳ ሹማምንቶች በሙሉ ይመክሩበታል ።ድማም ፣ ጎሽቶ፣ ገራድ፣ላዝማ ፣ አዝማ ፣ አዝማች፣ ሱልጣን ፣ ኢማም ተብለው የማዕረግ ሹመት ሲሰጣቸው ኢሎል ስፍራ በሚካሄደው የንግስና በዓል እውቅና ይሰጠዋል ።
ኢሎል ስፍራ የነገሱ እጅግ ብዙ ቢሆኑም በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቀውና ታሪኩ በስፋት የሚነገርላቸው ከድማም ጀምሮ እስከ ኢማም ናቸው።
ድማም በጋሞ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ናቸው በኋላም በህመም ምክንያ አልጋ ላይ ከዋሉ በኋላ ንግስናቸውን ለልጃቸው ቢሰጡትም አሻፈረኝ ብሎዋቸዋል።
ድማም በጋሞ እንዳረፉ ደፋሩ ጦረኛ የባዴ ልጅ ጎሽቶ ቀለምሶ ነገሰ ፡፡ የባለቤታቸውንም ጊስቶ የሚል የነግስና ስም ሰየመ ፡፡ በኋላም በአመታዊ ክብረ በአል ላይ ጎሽቶ ቀለምሶ በመሸነፍ ሀፍረት ተሰምቶት ሸሸ መንበረ ስልጣኑን ለሻዶ ልጅ ገራድ ባለከሽ አስረክበ ።
ገራድ ባለከሽም የባለቤታቸውን ስም “ጊስቶ” የሚለውን በመሻር ” ኢቴ ” የሚለውን ለሴቶች የንግስና ስም ሰየሙ ፡፡ ዛሬም ድረስ በመስቃን ማህበረሰብ ይህ መጠሪያ ለሴቶች የንግስና መጠሪያ ስም ነው ።
ሸሽተው የነበሩ ባዴና የባዴ ልጆች ከባዴ ህልፈት በኋላ ተመልሰው መጥተው ስልጣን ይገባናል ብለው የማጋውን የዳኝነቱን ስርአት እንዲመሩት ተደረገ እስከ ኢማም በድሩ ድረስ የማጋውን ስልጣን በባዴ ዘር ነው የነበረው።
ገራድ ካለፉ በኋላ የሳቸው አራተኛ ትውልድ የሆነው ላዝማ ማሬኖ ንግስናውን ተቀባ ፡፡ ላዝማ ማሬኖ ለረዥም ዘመን በንግስና ስማቸው የቆዩ ናቸው ፡፡ የላዝማ ወዳጅ ሼህ ኡስማን የነበሩት የራጋ ዳኝነትቱ ወይም በአሁኑ አጠራሩ ሰበር ሰሚ ችሎቱን(ፈራገዘኘ የባህላዊ የዳኝነት እና እርቅ ) ተሰጣቸው እውቀት ብቻ ሳይሆን ፍትሀዊም ነበሩ ። ከላዝማ ማሬኖ በኋላ አዝማ ሳሊሶ ተተኩ። አዝማ ሳሊሶ ጦረኛም ጠቢብም ነበሩ ይባላል ።

የጎሎቦ ተክል ድንጋይ
መገኛ አድራሻ ወረዳ፣ መስቃን ቀበሌ፣ምእራብ መስቃን የቦታው ልዩ ስም፣ ኢሎል ከቢዳራ ሜዳ ርቀት ፣2.5ኪሜ ከማእከል ቡታጂራ 12.5 ኪሜ ከቢዳራ ታዳጊ መዘጋጃ 3.5ኪሜ እድሜ ፣ 600አመታት በፊት

ቢዳራ ጠባ(ሜዳ)
17 ሄክታር ሜዳ ቦታ ሲሆን የፈረስ ጉግስ ውድድርና ልምምድ ማድረጊያ የነበረ ቦታ ነው፡፡ ቦታው ከየሰንጋውና ከየሞጣው (ከየክፍለህዝቡና ) ጀግኖች ለጦርነቶች ተመልምሎ ሚሰለጥኑበት ቦታ መሆኑን የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ልዩልዩ ውድድሮችና ትግሎች ሚደረግበት ሰርጎች፣ህዝባዊ ኩነቶችና ስብሰባዎች፣ ከኢሎል ንግስና በኋላ ባህላዊ በአላት ሚደረግበት ቦታ ከምእራብ ወደ ምስራቅ ሲታይ የኢቶብያ ካርታ ሚመስል፣ ከምስራቅ ወደ ምእራብ ደግሞ ሲታይ የአፍሪቻ ካርታ ምስል ያለው መሆኑ እና የማህበረሰቡ የተዋደቁ ጀግኖች መቃብሮች መገኛ ቦታ ነው፡፡ መገኛ አድራሻው ወረዳ፣ መስቃን ቀበሌ፣ምእራብ መስቃን ከቡታጂራ ርቀት፣ 10ኪሜ

ፏና ደን ወይም እሌና ደን
በፏና ደን ስር የሚከተሉት ነገሮች ይገኛሉ፡፡ ባህላዊ የንብ ቀፎዎች፣ የዱር እሰሳቶ ለምሳሌ ጦጣ፣ሚዳቆ፣አነር፣ዝንጀሮ፣ዘንዶ ይገኛሉ፡፡ የደኑ ስፋት . 67.25 ሄክታር ሲሆን በየተቦን ቀበሌ ይገኛል፡፡ Xy coordinate or GPS data የፏና ደን X{0420423} y{0898561} and X{0419497} Y{0898495

አምባ ደን
ቀበሌ፣ ምእራብ እምቦር የደኑ ስፋት፣ 57.75 ሀሄክታር ነው፡፡ Xy coordinate or GPS data of አመባ ፎርሰተ X{0420255} Y{0896967} and X{0421076} Y{0897235} ርቀት 13.5ኪሜ ከቡታጂራ
