የገና ጨዋታ በመስቃን ቤተ-ጉራጌ
ገና ማለት የኢየሱስ ልደት ነው ተብሎ የሚታመንበት በዓል ነው፤ የልደት በዓል መከበር የተጀመረው እንደጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ336 AD ላይ ነው የተጀመረው ። በየሀገሩ በሰፊው የሚከበር ክብረ በአል ሲሆን የየሀገራቱ ህግና ደንብ ይለያያል እንደ መስቃን ቤተ-ጉራጌ የራሱ የአከባበር ስርአት አለው የገና ጨዋታ በመስቃን ጉራጌ እንደማንኛውም ብሄረሠብ መንፈሳዊ በዓላትን ቢያከብርም አከባበሮቹ ላይ ግን የራሳቸው መንፈሳዊም ባህላዊ ህገ ደንብ አለው ። በመስቃን ጉራጌም የገና በዓል መስቃን መስቃን የሚሸቱ የራሱ የሆነ ልዩ መገለጫ ባለው መልኩ ይከበራል።የገና ጨዋታ የሚጀመረው ከዋናው የገና በዓል ቀን ከቀናቶች ቀድም ብሎ በየመንደሩ ትናንሽ ልጆች እየተመራረጡ በሚጫወቱት ጫወታ ይጀመራል።






ዋናዎቹ የገና በዓል ቀናት እስኪደርሱ ልጆች በየበራፋቸው እየተመራረጡ እርስ በእርስ የሚጫወቱ ሲሆን አዋቂዎች በበኩላቸው በነዚህ ወራት የመጫወቻ ገና (አንቃት) የሚያዘጋጁበት ሲሆን የመጨረሻዎቹ የገና ቀናት በጉጉትና በተስፋ የሚጠብቁበት ነው። ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውና በአዋቂዎች ጭምር የሚደምቀው የገና በዓል ቀናት የዋዜማውለት የሚከበረው የልጆች ገና(እንስ ገና) እንዲሁም ዋናው ገና(ልቅ ገና) ናቸው።ሩሩ የሚመታበት የገና ዱላ ከወደቂጡ የታጠፈና እንጨት ሲሆን በጉራጊኛ “አንቃት” ይባላል። አንቃት (የገና ዱላ) የሚዘጋጀው ማንኛውም ከዘራ በሚመስል ጠንካራ እንጨት ነው።በቅርፅ ክብ የሆነውና እንደ ኳስ ተጫዋቾች በቡድን በመጫወቻ ዱላቸው እየተቀባበሉ/እየለጉ የሚጫወቱበት ቁስ በአማርኛ “ውር ውር”ሲባል በጉራጊኛ ትኩስ (እንኩብኩብ) ይባላል። ውርውር (እንኩብኩብ) በማይፈረፈር ጠንካራ እንጨት በተለምዶ እንደ “ጥሙጋ” ፣ጥቁር እንጨት(ገሬባ) ፣ወይራ፣ባህር ዛፍ፣ገድራና የመሳሰሉትን የተለያዩ ስለት ያላቸው ነገሮች ተጠቅሞ ክብ በማድረግ የሚዘጋጅ ሲሆን አሁን አሁን የተጣለ ፕላስቲክ ነክ ቁሳቁሶች አቅልጦ በማድቦልቦል የሚዘጋጅ ነው። በገና ጨዋታ በዓል የዋዜማ ቀን “የልጆች ገና ቀን” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በዚህ ቀን በየቤቱ የገብስ ቆሎ ይዘጋጃል። ልጆች በየቤቱ እየተዟዟሩ የገና ቆሎው ይበላሉ። በመጨረሻውና በዋናው የገና በዓል እለት ጠዋት የገና ጨዋታ መጫወቻ ሠዓት ከመድረሱ በፊት ልክ አስራ ሁለት ሠዓት አካባቢ የአንድ አካባቢ ሴት ልጃ ገረዶች ልጆች(ሴቶች)ከየቤታቸው ቆሎ፣ ስከር (ጠላ)፣እና አንጢፍት (ወንፊት) ይዘው በመምጣት አበጋዝነት/አዝማችነት በታሰረበት ትልቅ ዛፍ ስር ወይም ሰፈራቸው በሚገኝ አድባር ቦታ ተሰብስበው ልጃገረዶች እመወር እምወር ወግቤእምወር እምወር ወግቤእምወር…..ይላሉ።ልጃ ገረዶቹ “እምወር እምወር ወግቤ እምወር…”በሚሉበት ወቅት ወንፊቱ (አንጢፋት)ገልብጠው በቆሎው ላይበማድረግ ክብ ሠርተውእምወር እምወር ወግቤእምወር ወግቤ(2*)፣የዳኮኛ ጠላት ተክቤ እምወር ወግቤ፣እምወር እምወር ወግቤ እምወር፣ወግቤ የእመኝ ጠላት ተክቤ።እያሉ በሚያምር ዜማ ያደምቁታል።ወጣት ወንዶች ወግቤ በሚባልበት ቦታ ተግኝተው ሴቶቹ ያመጡት ቆሎ እየበሉ ይጫወታሉ። ወንዶቹ የወግቤ እምወር ፕሮግራም ከጨረሱበኃላ ቆሎው በልተው፣ጠላው ጠጥተው ከጨረሱ በኃላ ሳይለያዩ ተጨማሪ ገና የሚጫወቱ ወጣቶች በመጨመር የገና ዱላ(አንቃት) ይዘው ወደ አቅራቢያው የገና መጫወቻ ቦታ ይሄዳሉ።
.
