quote 1.png

ባህላዊ ምግብና አዘገጃጀት

የመስቃን ቤተ-ጉራጌ ባህላዊ ምግቦች የሚዘጋጁት ከስጋ፣ከወተት ተዋፅኦ፣ከጎመን፣ከእህል ዘሮች እና ከእንሰት ተዋፅኦ ወዘተ ሲሆን የተለያዩ ባህላዊ ዘዴዎችን በመጠቀም በተለያየ መልኩ ይሰራሉ፡፡ ለዛሬ ጥቂቶቹን እናስተዋውቃችሁ

አሻሻት አሻሻት

የተዘጋጀ ነጭ ቆጮ በእንጨት ገበቴ በደንብ ታሽቶና ቦክቶ በቆጮ መጠፍጠፊያ በቀጭኑ ከተዘጋጀ በኋላ እንዳያር በምጣድ እያገለበጡ በመጋገር ወይ በትኩሱ አሊያም በቆጮ ቅጠል ጠቅልለው ዩሳዶረ/ይወደረ/ በሚባል ከቃጫና ከአክርማ በሚሰራው ቁስ ጠቅልለው በማቀዝቀዝ ከተዘጋጀው ማባያ ጋር ይበላል፡፡ ፡-

አሻሻት አሻሻትClose

ዳፑየ/ዳፗ/፡-

ነጭ ቆጮ በገበቴ ውስጥ በውሀ እየለሰለሰ በሀይል ቦክቶ በምጣድ ላይ በቀጭኑ የተተለተለ የእንሰት ኮባና ቅጠል በመጎዝጎዝ በኋላም ሊጡን በማፍሰስ ከተስተካከለ በኋላ በላዩም ከስር የተነጠፈው ዓይነት የተተለተለ ኮባና ቅጠል እንዲለብስ ተደርጎ ሌላ ሁለተኛ ምጣድ ተደፍቶበት ከታች እያነደዱበት በእንፋሎት ብቻ እንዲበስል የሚደረግ ሲሆን የመብሰያ ሰዓቱ ሲደርስ ከምድጃ አውጥተው ሽፋኑን አላቀው እንዲቀዘቅዝ በማድረግ በዝማሟጃት በቆቆስየና በካሽየ የሚበላ ባህላዊ ምግብ ነው፡፡ /ዳፗ /፡-

ዳፑየ/ዳፗ/፡-Close

አልባቦጫት፡-

ከአሻሻት የሚለየው ቡኮው በጣም በማቅጠን በጣም ስስ ሆኖ ፊቱና ጀርባው በእንሰት ቅጠል ተሸፍኖ የምጣዱ አካል ሳይነካው የሚበስል ሲሆን በበዓላት ቀን በስጋ ክትፎ ወይም በጎመን ክትፎ ቀርቦ የሚበላ ተመራጩ ቆጮ ነው፡፡ ፡-

አልባቦጫትClose

ቅሙስ

አብዛኛውን ጊዜ የሚዘወተረው አንድም በፆም ወቅት አሊያም የሆድ ህመም/ማስቀመጥ/ የገጠመው ቤተሰብ ሲኖር ሲሆን ነጭ ቆጮ ላይ ትንሽ የስንዴ ወይም የበቆሎ ዱቄት ብን አርጎ በደረቁ በማሸት በወፍራሙ በምጣድ ላይ በማብሰል ደረቅ/ጠንከር/ እንዲል ከተገላበጠ በኋላ ሲበስል ከምጣድ በማውጣት ተቆራርሶ ብዙም ሳይበርድ ለፆም በተዘጋጀ የማባያ አይነት የሚበላ ባህላዊ ምግብ ነው፡፡ ፡-

 

ቅሙስClose
food2
food3
food5