የኢደል አደሀ ሰላት



የሴቶች አረፋ አከባበር
“የአረፋ ገባተውታን የፍቸ ቅረረውታን ኸማ ድመቆ”
የሴቶች አረፋ በመስቃን ወረዳ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ አከባበር በዙልሂጃ በ9ኛዉ ቀን (አረፋ) ሁሉም ሁጃጆች በሙሉ አርዱል አረፋ ላይ ዉቁፍ ለማድረግ ሲሄዱ ሀጅ የማያደርጉ የመካ ወንዶችም ለመኻደም ይሄዳሉ።በዛን ጊዜ ሀረሙ በጠቅላላ ባዶ ሲሆን ቀኑን ሙሉ ሀረሙ የሴቶች ብቻ እስኪመስል ድረስ በሴቶች ይጥለቀለቅ ነበር፣ የማፍጠሪያ ምግብም አዘጋጅተዉ የመካ ሴቶች ናቸዉ ቀኑን እስከ ምሽት ድረስ ሀረሙን ሞልተዉ ካዕባዉን ከበዉ በኢባዳ ስለሚያሳልፉ የሴቶች የመካ አረፋ የሚል ስያሜ ተሠጠዉ።ያን (ባህል) በየሀገሩ እየመጣ በተለያየ አከባበር የሴቶች አረፋ በሚል ስያሜ ይከበራል።ህዚህም ወረዳችን ላይ የእናቶች ዝግጅት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።እናቶች ቆጮ ከመፋቅ እስከ መጋገር፣ ቅቤ በማዘጋጀት፣ሚጥሚጣ በመውቀጥና ጎመን በመቀቀል ትኩረት ሰጥተው ሲሰሩ ሴት ልጃ ገረዶች ደግሞ የመኖሪያ ቤቶችን በማስዋብ፣ የመመገቢያ ቁሶችን በማፅዳት፣ የቤተሰቡን አልባሳት ሁሉ በማጠብና ሌሎች ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በሚያሟሉ ስራዎች ላይ ይጠመዳሉ፡፡የሴቶች አረፋ ከዋናው አረፋ በዓል በዋዜማው የሚከበር በዓል ሲሆን በዚህ ዕለት ሴቶች የበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋግጡበት ቀን ነው፡፡በዚሁ እለት ሴቶች የጎመን ክትፎ እና ዝሟሙጃት በማዘጋጀት እንዲሁም የቅቤ ቡና በማፍላት ቤተ-ዘመድና ጎረቤት ጠርተው በፍቅር የሚገባበዙበት፣የሚደሰቱበትና ”የአረፋ ገባተውታን የፍቸ ቅረረውታን ኸማ ድመቆ”ብለው እየተመራረቁ የሚያሳልፍት ደማቅ በዓል ነው፡፡








