የመስቃን ወረዳ ምክር ቤት
የጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
ዓላማ
በዞን ምክርቤት ጽ/ቤትና በየደረጃው ባሉ ምክርቤት ጽ/ቤቶች ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ተመስርተው በተቀናጀና ሁሉ አቀፍ በሆነ እቅድ የሚመሩበት አሰራር ስርዓት መዘርጋት ነው፡፡
ራዕይ
“እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2022 ለዲሞክራሲያዊና መልካም አስተዳደር መስፈን አርአያ የሆነ ምክር ቤት መሆን፣ ይህን ራዕይ ለማሳካት ምክር ቤቱ የሚከተሉትን ሃላፊነቶቹን ለመወጣት ይተጋል
- ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤
- የህዝብን መብትና ጥቅም ሊያረጋግጡ እና ከለላ ሊሆኑ የሚችሉ ህጎችን ማውጣት፤
- የግለሠቦችን የኑሮ ደረጃ ተጨባጭ በሚባል ሁኔታ ሊያሻሽልና ድህነትን በሁሉም መገለጫ የሚቀንስ አፈፃፀምን ራዳ እንዲሰፍን ማድረግ፤
- በመንግሰት የሚነደፉ የልማት ዕቅዶች የዋጋ ንረትንና ሥራ አጥነትን መቀነስ ላይ አተኩረው እንዲቀየሱና እንዲፈፀሙ መከታተልና በተገቢው የህግ ማዕቀፍ እንዲታገዝ ማድረግ፤
- ጠንካራ እና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ የክትትል ቁጥጥር ስራ ማድረግ፤
የወረዳ መንግስት በጀት መርምሮ ማፅደቅ እና የህዝብ ውክልና ተግባርን የህዝብ አመኔታን የሚፈጥር አድርጎ መስራት ሲሆን፣ የሚከተሉትም ከላይ የቀረበው ራዕይ ለማሳካት የሚጣሉ ስትራቴጂኪዊ ግቦች ይሆናሉ፡፡
ተልዕኮ
የምክር ቤቱን አሰራር በማሻሻል፣ በህብረተሰቡ የነቃ ተሣትፎ ለዞኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት መፋጠን ፋይዳ ያላቸውን ህጎች በማውጣት፣ አፈጻጸማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር እና ቁርጠኛ የመንግስት አካላትን በማደራጀት የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እንዲጎለብት፣ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት አሠራር እንዲሰፍን እና ዴሞኪራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት ማድረግ ነው::ለዚህ የምክር ቤት ተልኮም የሚከተሉት ጉዳዮች ላይ አፅንዖት አድርጎ የሚሠራ ይሆናል፤-
- ምክር ቤቱ የወከለው ህዝብ ተጠቃሚነትና ፍላጎት የሚስተጋባበት እንዲሆን፣ ለዚህም ከጎኑ የሚሆን ህዝብ የመፍጠር እና የህዝብ ዕድገት ፍላጎቶች እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ማሳየት፣
- ውጤታማ የሆነ በአስፈፃሚ አካላት ላይ የክትትል ቁጥጥር በማድረግ ከህዝብ ፍላጎት ያፈነገጡ ማነቆዎች እንዲወገዱ ማድረግ፣
- የወረዳዉ ህዝቦች በሚወጡ ህጎች ላይ ሰፊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ
- በሶስቱ የመንግሰቱ አካለት መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት በመፍጠር፣ ግንኙነታቸው ውጤታማና ቅልጥፋና ያለው እንዲሆን ማድረግ
- አዳዲስ ሀሳቦች የማስተዋወቅ፣ የለውጥ አሰራር የተዘረጋበት እና የህዝብ ጥያቄዎች የሚደመጡበት ምክር ቤታዊ አገልግሎትና አስተዳደር በመስጠት የምክር ቤት አባላት ህገመንግስታዊ ሀላፊነታቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲወጡ ማስቻል፣
